وَٱلۡوَزۡنُ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡحَقُّۚ فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው፡፡


وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُم بِمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَظۡلِمُونَ

ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ ተአምራቶቻችንን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡


وَلَقَدۡ مَكَّنَّـٰكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَجَعَلۡنَا لَكُمۡ فِيهَا مَعَٰيِشَۗ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

በምድርም ላይ በእርግጥ አስመቸናችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ለናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ፤ ምስጋናችሁ በጣም ጥቂት ነው፡፡


وَلَقَدۡ خَلَقۡنَٰكُمۡ ثُمَّ صَوَّرۡنَٰكُمۡ ثُمَّ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ لَمۡ يَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِينَ

በእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክቶች «ለአዳም ስገዱ» አልን፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡


قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسۡجُدَ إِذۡ أَمَرۡتُكَۖ قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ

(አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡ «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡


قَالَ فَٱهۡبِطۡ مِنۡهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخۡرُجۡ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّـٰغِرِينَ

ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፡፡



الصفحة التالية
Icon