وَقَالَتۡ أُولَىٰهُمۡ لِأُخۡرَىٰهُمۡ فَمَا كَانَ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلٖ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ

«መጀመሪያይቱም ለኋለኛይቱ ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም» ትላለች፡፡ «ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ» (ይላቸዋል)፡፡


إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمۡ أَبۡوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلۡجَمَلُ فِي سَمِّ ٱلۡخِيَاطِۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُجۡرِمِينَ

እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ ገነትን አይገቡም፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡


لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٞ وَمِن فَوۡقِهِمۡ غَوَاشٖۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّـٰلِمِينَ

ለእነርሱ ከገሀነም እሳት (በሥራቸው) ምንጣፍ ከበላያቸውም (የእሳት) መሸፈኛዎች አሏቸው፡፡ እንደዚሁም በደለኞችን እንቀጣለን፡፡


وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَآ أُوْلَـٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

እነዚያም ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድምና፤ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡


وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلّٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهۡتَدِيَ لَوۡلَآ أَنۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُۖ لَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّۖ وَنُودُوٓاْ أَن تِلۡكُمُ ٱلۡجَنَّةُ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

በደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፡፡ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፡፡ «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፡፡ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ፡፡ ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡



الصفحة التالية
Icon