قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَلِأَخِي وَأَدۡخِلۡنَا فِي رَحۡمَتِكَۖ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّـٰحِمِينَ

(ሙሳም)፡- «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወንድሜም ማር፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡


إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ ٱلۡعِجۡلَ سَيَنَالُهُمۡ غَضَبٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَذِلَّةٞ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُفۡتَرِينَ

እነዚያ ወይፈኑን (አምላክ አድርገው) የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ፤ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል፡፡ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን፡፡


وَٱلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ثُمَّ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِهَا وَءَامَنُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ

እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡


وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى ٱلۡغَضَبُ أَخَذَ ٱلۡأَلۡوَاحَۖ وَفِي نُسۡخَتِهَا هُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ هُمۡ لِرَبِّهِمۡ يَرۡهَبُونَ

ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ፡፡


وَٱخۡتَارَ مُوسَىٰ قَوۡمَهُۥ سَبۡعِينَ رَجُلٗا لِّمِيقَٰتِنَاۖ فَلَمَّآ أَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ قَالَ رَبِّ لَوۡ شِئۡتَ أَهۡلَكۡتَهُم مِّن قَبۡلُ وَإِيَّـٰيَۖ أَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَّآۖ إِنۡ هِيَ إِلَّا فِتۡنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَآءُ وَتَهۡدِي مَن تَشَآءُۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَاۖ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡغَٰفِرِينَ

ሙሳም ከሕዝቦቹ ውስጥ ለቀጠሮዋችን ሰባን ሰዎች መረጠ፡፡ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በያዘቻቸውም ጊዜ ሙሳ አለ «ጌታዬ ሆይ! በሻህ ኖሮ ከአሁን በፊት በአጠፋሃቸው ነበር፡፡ እኔንም (ባጠፋኸኝ ነበር)፡፡ ከእኛ ቂሎቹ በሠሩት ነገር ታጠፋናለህን እርሷ (ፈተናይቱ) ያንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ፡፡ የምትሻውንም ታቀናለህ፡፡ አንተ ረዳታችን ነህና ለእኛ ምሕረት አድርግልን፡፡ እዘንልንም፡፡ አንተም ከመሓሪዎች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»



الصفحة التالية
Icon