وَمِن قَوۡمِ مُوسَىٰٓ أُمَّةٞ يَهۡدُونَ بِٱلۡحَقِّ وَبِهِۦ يَعۡدِلُونَ
ከሙሳም ሕዝቦች በእውነት የሚመሩት በእርሱም (ፍርድን) የሚያስተካክሉ ጭፍሮች አሉ፡፡
وَقَطَّعۡنَٰهُمُ ٱثۡنَتَيۡ عَشۡرَةَ أَسۡبَاطًا أُمَمٗاۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسۡتَسۡقَىٰهُ قَوۡمُهُۥٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡحَجَرَۖ فَٱنۢبَجَسَتۡ مِنۡهُ ٱثۡنَتَا عَشۡرَةَ عَيۡنٗاۖ قَدۡ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٖ مَّشۡرَبَهُمۡۚ وَظَلَّلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡغَمَٰمَ وَأَنزَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰۖ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ
ዐሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ (መታውም) ከእርሱ ዐሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ በእነሱም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእነሱም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን፡፡ «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ» (አልን፤ ጸጋችንን በመካዳቸው) አልበደሉንምም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
وَإِذۡ قِيلَ لَهُمُ ٱسۡكُنُواْ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةَ وَكُلُواْ مِنۡهَا حَيۡثُ شِئۡتُمۡ وَقُولُواْ حِطَّةٞ وَٱدۡخُلُواْ ٱلۡبَابَ سُجَّدٗا نَّغۡفِرۡ لَكُمۡ خَطِيٓـَٰٔتِكُمۡۚ سَنَزِيدُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
ለእነርሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) «በዚህች ከተማ ተቀመጡ፡፡ ከእርሷም በሻችሁት ስፍራ ብሉ፡፡ (የምንፈልገው) የኃጢኣታችንን መርገፍ ነው በሉም፡፡ የከተማይቱንም በር አጎንብሳችሁ ግቡ፡፡ ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና፡፡ በጎ ለሠሩት በእርግጥ እንጨምራለን፡፡»
فَبَدَّلَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡ قَوۡلًا غَيۡرَ ٱلَّذِي قِيلَ لَهُمۡ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِجۡزٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُواْ يَظۡلِمُونَ
ከእነሱም ውስጥ እነዚያ (ራሳቸውን) የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የኾነን ቃል ለወጡ፡፡ በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል መዐትን ከሰማይ ላክንባቸው፡፡