وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ

ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ፡፡


يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَتَّقُواْ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّكُمۡ فُرۡقَانٗا وَيُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡


وَإِذۡ يَمۡكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيُثۡبِتُوكَ أَوۡ يَقۡتُلُوكَ أَوۡ يُخۡرِجُوكَۚ وَيَمۡكُرُونَ وَيَمۡكُرُ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ

እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡


وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا قَالُواْ قَدۡ سَمِعۡنَا لَوۡ نَشَآءُ لَقُلۡنَا مِثۡلَ هَٰذَآ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

አንቀጾቻችንም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡


وَإِذۡ قَالُواْ ٱللَّهُمَّ إِن كَانَ هَٰذَا هُوَ ٱلۡحَقَّ مِنۡ عِندِكَ فَأَمۡطِرۡ عَلَيۡنَا حِجَارَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ أَوِ ٱئۡتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٖ

«ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ (የተወረደ) እውነት እንደ ኾነ በኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን» ባሉም ጊዜ (አስታውስ)



الصفحة التالية
Icon