وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ أَن يُفۡتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصۡدِيقَ ٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَتَفۡصِيلَ ٱلۡكِتَٰبِ لَا رَيۡبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡


أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ فَأۡتُواْ بِسُورَةٖ مِّثۡلِهِۦ وَٱدۡعُواْ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡


بَلۡ كَذَّبُواْ بِمَا لَمۡ يُحِيطُواْ بِعِلۡمِهِۦ وَلَمَّا يَأۡتِهِمۡ تَأۡوِيلُهُۥۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّـٰلِمِينَ

ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡


وَمِنۡهُم مَّن يُؤۡمِنُ بِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن لَّا يُؤۡمِنُ بِهِۦۚ وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُفۡسِدِينَ

ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡


وَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل لِّي عَمَلِي وَلَكُمۡ عَمَلُكُمۡۖ أَنتُم بَرِيٓـُٔونَ مِمَّآ أَعۡمَلُ وَأَنَا۠ بَرِيٓءٞ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ

«ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡



الصفحة التالية
Icon