قُلِ ٱنظُرُواْ مَاذَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَا تُغۡنِي ٱلۡأٓيَٰتُ وَٱلنُّذُرُ عَن قَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ

«በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡


فَهَلۡ يَنتَظِرُونَ إِلَّا مِثۡلَ أَيَّامِ ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلِهِمۡۚ قُلۡ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ

የእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡


ثُمَّ نُنَجِّي رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ كَذَٰلِكَ حَقًّا عَلَيۡنَا نُنجِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን፡፡ እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ፡፡


قُلۡ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمۡ فِي شَكّٖ مِّن دِينِي فَلَآ أَعۡبُدُ ٱلَّذِينَ تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِنۡ أَعۡبُدُ ٱللَّهَ ٱلَّذِي يَتَوَفَّىٰكُمۡۖ وَأُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

«እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡


وَأَنۡ أَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفٗا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡


وَلَا تَدۡعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَۖ فَإِن فَعَلۡتَ فَإِنَّكَ إِذٗا مِّنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ

«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡



الصفحة التالية
Icon