وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ

ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፡፡ (አላቸውም)፡- «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ነኝ፡፡»


أَن لَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ أَلِيمٖ

«አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና፡፡»


فَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا نَرَىٰكَ إِلَّا بَشَرٗا مِّثۡلَنَا وَمَا نَرَىٰكَ ٱتَّبَعَكَ إِلَّا ٱلَّذِينَ هُمۡ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ ٱلرَّأۡيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلِۭ بَلۡ نَظُنُّكُمۡ كَٰذِبِينَ

ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት መሪዎቹ ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም፡፡ እነዚያም እነሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም፡፡ ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም፡፡ ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን አሉ፡፡


قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتۡ عَلَيۡكُمۡ أَنُلۡزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمۡ لَهَا كَٰرِهُونَ

«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ (ነብይነት) ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለርቯ ጠይዎች ስትሆኑ እርቯን (በመቀበል) እናስገድዳችኋለን» አላቸው፡፡


وَيَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مَالًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۚ وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْۚ إِنَّهُم مُّلَٰقُواْ رَبِّهِمۡ وَلَٰكِنِّيٓ أَرَىٰكُمۡ قَوۡمٗا تَجۡهَلُونَ

«ሕዝቦቼም ሆይ! በርሱ (በተላክሁበት ማድረስ) ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እኔም እነዚያን ያመኑትን አባራሪ አይደለሁም፡፡ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ ናቸውና፡፡ ግን እኔም የምትሳሳቱ ሕዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ፡፡»



الصفحة التالية
Icon