قَالُواْ يَٰصَٰلِحُ قَدۡ كُنتَ فِينَا مَرۡجُوّٗا قَبۡلَ هَٰذَآۖ أَتَنۡهَىٰنَآ أَن نَّعۡبُدَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِي شَكّٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ مُرِيبٖ

«ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ፡፡


قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي مِنۡهُ رَحۡمَةٗ فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِنۡ عَصَيۡتُهُۥۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيۡرَ تَخۡسِيرٖ

«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው፡፡


وَيَٰقَوۡمِ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٞ قَرِيبٞ

ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት፡፡ ተውዋትም፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» (አላቸው)፡፡


فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُواْ فِي دَارِكُمۡ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٖۖ ذَٰلِكَ وَعۡدٌ غَيۡرُ مَكۡذُوبٖ

ወግተው ገደሏትም፡፡ (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ፡፡ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው፡፡


فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا صَٰلِحٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَمِنۡ خِزۡيِ يَوۡمِئِذٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ

ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን፡፡ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፡፡ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና፡፡



الصفحة التالية
Icon