قُلۡ فَأۡتُواْ بِكِتَٰبٖ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ هُوَ أَهۡدَىٰ مِنۡهُمَآ أَتَّبِعۡهُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
«ከአላህ ዘንድ የኾነን መጽሐፍ እርሱ ከሁለቱም ይበልጥ ቅን የኾነን አምጡ፡፡ እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ብታመጡት) እከተለዋለሁ» በላቸው፡፡
فَإِن لَّمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَكَ فَٱعۡلَمۡ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهۡوَآءَهُمۡۚ وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّنِ ٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ بِغَيۡرِ هُدٗى مِّنَ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّـٰلِمِينَ
እሺ ባይሉህም፤ የሚከተሉት፤ ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ አላህ በደለኞች ሕዝቦችን አይመራምና፡፡
۞وَلَقَدۡ وَصَّلۡنَا لَهُمُ ٱلۡقَوۡلَ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
ይገሰጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን፡፡
ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِهِۦ هُم بِهِۦ يُؤۡمِنُونَ
እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ፡፡
وَإِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِهِۦٓ إِنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّنَآ إِنَّا كُنَّا مِن قَبۡلِهِۦ مُسۡلِمِينَ
በእነሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡
أُوْلَـٰٓئِكَ يُؤۡتَوۡنَ أَجۡرَهُم مَّرَّتَيۡنِ بِمَا صَبَرُواْ وَيَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ
እነዚያ በመታገሳቸው ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይስሰጣሉ፡፡ ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፡፡ ከሰጠናቸውም ሲሳይ ይለግሳሉ፡፡