أَئِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلرِّجَالَ وَتَقۡطَعُونَ ٱلسَّبِيلَ وَتَأۡتُونَ فِي نَادِيكُمُ ٱلۡمُنكَرَۖ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱئۡتِنَا بِعَذَابِ ٱللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّـٰدِقِينَ

«እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን» (አላቸው)፡፡ የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡


قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

«ጌታዬ ሆይ! በአመጸኞች ሕዝቦች ላይ እርዳኝ» አለ፡፡


وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَآ إِبۡرَٰهِيمَ بِٱلۡبُشۡرَىٰ قَالُوٓاْ إِنَّا مُهۡلِكُوٓاْ أَهۡلِ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةِۖ إِنَّ أَهۡلَهَا كَانُواْ ظَٰلِمِينَ

መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት፡፡


قَالَ إِنَّ فِيهَا لُوطٗاۚ قَالُواْ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَن فِيهَاۖ لَنُنَجِّيَنَّهُۥ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

«በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ» አላቸው፡፡ «እኛ በውስጧ ያለውን ይበልጥ ዐዋቂ ነን፡፡ (እርሱን) በእርግጥ እናድነዋለን፡፡ ቤተሰቦቹንም ጭምር፡፡ ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከሚቀሩት ናት» አሉት፡፡


وَلَمَّآ أَن جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗاۖ وَقَالُواْ لَا تَخَفۡ وَلَا تَحۡزَنۡ إِنَّا مُنَجُّوكَ وَأَهۡلَكَ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነሱ ምክንያት አዘነ፡፡ በእነርሱም ልቡ ተጨነቀ፡፡ «አትፍራ፤ አትዘንም፡፡ እኛ አዳኞችህ ነን፡፡ ቤተሰቦችህንም፤ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ ናት» አሉትም፡፡



الصفحة التالية
Icon