إِن تُبۡدُواْ شَيۡـًٔا أَوۡ تُخۡفُوهُ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት (በርሱ ይመነዳችኋል)፡፡ አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡


لَّا جُنَاحَ عَلَيۡهِنَّ فِيٓ ءَابَآئِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآئِهِنَّ وَلَآ إِخۡوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآءِ إِخۡوَٰنِهِنَّ وَلَآ أَبۡنَآءِ أَخَوَٰتِهِنَّ وَلَا نِسَآئِهِنَّ وَلَا مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُنَّۗ وَٱتَّقِينَ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدًا

(የነቢዩ ሚስቶች) በአባቶቻቸው፣ በወንዶች ልጆቻቸውም፣ በወንድሞቻቸውም፣ ወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ በእኅቶቻቸው ወንዶች ልጆችም፣ (ምእምናት በኾኑት) በሴቶቻቸውም፣ እጆቻቸው በጨበጧቸውም ባሮች (አጠገብ በመገለጥ) በእነርሱ ላይ ኃጢአት የለባቸውም፡፡ (ሴቶች ሆይ! ታዘዙ) አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነውና፡፡


إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِيِّۚ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيۡهِ وَسَلِّمُواْ تَسۡلِيمًا

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡


إِنَّ ٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَأَعَدَّ لَهُمۡ عَذَابٗا مُّهِينٗا

እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚያስከፉ በቅርቢቱ ዓለም በመጨረሻይቱም አላህ ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም አዋራጅን ቅጣት ደግሶላቸዋል፡፡


وَٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ بِغَيۡرِ مَا ٱكۡتَسَبُواْ فَقَدِ ٱحۡتَمَلُواْ بُهۡتَٰنٗا وَإِثۡمٗا مُّبِينٗا

እነዚያንም ምእምናንንና ምእምናነትን ባልሰሩት ነገር (በመዝለፍ) የሚያሰቃዩ ዕብለትንና ግልጽ ኃጢአትን በእርግጥ ተሸከሙ፡፡



الصفحة التالية
Icon