وَقَالُواْ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ

«ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት መጽሐፋችንን አስቸኩልልን» አሉም፡፡


ٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلۡأَيۡدِۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ

በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡


إِنَّا سَخَّرۡنَا ٱلۡجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحۡنَ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِشۡرَاقِ

እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋድም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆኑ ገራንለት፡፡


وَٱلطَّيۡرَ مَحۡشُورَةٗۖ كُلّٞ لَّهُۥٓ أَوَّابٞ

በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው (ገራንለት)፡፡ ሁሉም ለእርሱ (ማወደስ) የሚመላለስ ነው፡፡


وَشَدَدۡنَا مُلۡكَهُۥ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡحِكۡمَةَ وَفَصۡلَ ٱلۡخِطَابِ

መንግሥቱንም አበረታንለት፡፡ ጥበብንም ንግግርን መለየትንም ሰጠነው፡፡


۞وَهَلۡ أَتَىٰكَ نَبَؤُاْ ٱلۡخَصۡمِ إِذۡ تَسَوَّرُواْ ٱلۡمِحۡرَابَ

የተከራካሪዎቹም ወሬ መጥቶልሃልን? ምኩራቡን በተንጠላጠሉ ጊዜ፡፡


إِذۡ دَخَلُواْ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنۡهُمۡۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ خَصۡمَانِ بَغَىٰ بَعۡضُنَا عَلَىٰ بَعۡضٖ فَٱحۡكُم بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَلَا تُشۡطِطۡ وَٱهۡدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ

በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም በደነገጠ ጊዜ «አትፍራ፤ (እኛ) ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን፡፡ በመካከላችንም በእውነት ፍረድ፡፡ አታዳላም፡፡ ወደ መካከለኛውም መንገድ ምራን፤» አሉት፡፡



الصفحة التالية
Icon