وَلَوۡ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفۡتَدَوۡاْ بِهِۦ مِن سُوٓءِ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَبَدَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يَكُونُواْ يَحۡتَسِبُونَ

ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል፡፡


وَبَدَا لَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

ለእነርሱም የሠሩዋቸው መጥፎዎቹ ይገለጹላቸዋል፡፡ በእነርሱም ላይ በእርሱ ያላግጡበት የነበሩት ቅጣት ይሰፍርባቸዋል፡፡


فَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ضُرّٞ دَعَانَا ثُمَّ إِذَا خَوَّلۡنَٰهُ نِعۡمَةٗ مِّنَّا قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلۡمِۭۚ بَلۡ هِيَ فِتۡنَةٞ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

ሰውም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ይጠራናል፡፡ ከዚያም ከእኛ የኾነውን ጸጋ በሰጠነው ጊዜ «እርሱን የተሰጠሁት፤ በዕውቀት ብቻ ነው» ይላል፡፡ ይልቁንም እርሷ (ጸጋይቱ) መፈተኛ ናት፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡


قَدۡ قَالَهَا ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብለዋታል፡፡ ይሠሩት የነበሩትም ነገር ከእነርሱ አልጠቀማቸውም፡፡


فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْۚ وَٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡ هَـٰٓؤُلَآءِ سَيُصِيبُهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا كَسَبُواْ وَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ

የሠሩዋቸውም መጥፎዎች (ቅጣት) አገኛቸው፡፡ ከእነዚህም እነዚያ የበደሉት የሠሩዋቸው መጥፎዎች (ፍዳ) በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡ እነርሱም አምላጮች አይደሉም፡፡



الصفحة التالية
Icon