قُلۡ أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَأۡمُرُوٓنِّيٓ أَعۡبُدُ أَيُّهَا ٱلۡجَٰهِلُونَ

«እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድግገዛ ታዙኛላችሁን?» በላቸው፡፡


وَلَقَدۡ أُوحِيَ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ لَئِنۡ أَشۡرَكۡتَ لَيَحۡبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡


بَلِ ٱللَّهَ فَٱعۡبُدۡ وَكُن مِّنَ ٱلشَّـٰكِرِينَ

ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡


وَمَا قَدَرُواْ ٱللَّهَ حَقَّ قَدۡرِهِۦ وَٱلۡأَرۡضُ جَمِيعٗا قَبۡضَتُهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَٱلسَّمَٰوَٰتُ مَطۡوِيَّـٰتُۢ بِيَمِينِهِۦۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

አላህንም በትንሣኤ ቀን ምድር በመላ ጭብጡ ስትኾን፤ ሰማያትም በኀይሉ የሚጠቀለሉ ሲኾኑ (ከርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው) ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ ከሚያጋሩት ጠራ፤ ላቀም፡፡


وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخۡرَىٰ فَإِذَا هُمۡ قِيَامٞ يَنظُرُونَ

በቀንዱም ይንነፋል፡፡ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡርና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ (መንነፋት) ይንነፋል፡፡ ወዲያውም እነርሱ (የሚሠራባቸውን) የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ፡፡


وَأَشۡرَقَتِ ٱلۡأَرۡضُ بِنُورِ رَبِّهَا وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ وَجِاْيٓءَ بِٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَقُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፡፡ መጽሐፉም ይቅቀረባል፡፡ ነቢያቱና ምስክሮቹም ይመጣሉ፡፡ በመካከላቸውም በእውነት ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡



الصفحة التالية
Icon