فَوَقَىٰهُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِ مَا مَكَرُواْۖ وَحَاقَ بِـَٔالِ فِرۡعَوۡنَ سُوٓءُ ٱلۡعَذَابِ
ከመከሩዋቸውም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው፡፡
ٱلنَّارُ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا غُدُوّٗا وَعَشِيّٗاۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدۡخِلُوٓاْ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ أَشَدَّ ٱلۡعَذَابِ
እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትኾንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት (ገሀነምን) አግቡዋቸው» (ይባላል)፡፡
وَإِذۡ يَتَحَآجُّونَ فِي ٱلنَّارِ فَيَقُولُ ٱلضُّعَفَـٰٓؤُاْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُنَّا لَكُمۡ تَبَعٗا فَهَلۡ أَنتُم مُّغۡنُونَ عَنَّا نَصِيبٗا مِّنَ ٱلنَّارِ
በእሳትም ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ደካማዎቹም ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ (አሁን) ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ፡፡
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُلّٞ فِيهَآ إِنَّ ٱللَّهَ قَدۡ حَكَمَ بَيۡنَ ٱلۡعِبَادِ
እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን፡፡ አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈረደ» ይላሉ፡፡
وَقَالَ ٱلَّذِينَ فِي ٱلنَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ٱدۡعُواْ رَبَّكُمۡ يُخَفِّفۡ عَنَّا يَوۡمٗا مِّنَ ٱلۡعَذَابِ
እነዚያም በእሳት ውሰጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን» ይላሉ፡፡
قَالُوٓاْ أَوَلَمۡ تَكُ تَأۡتِيكُمۡ رُسُلُكُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ قَالُواْ بَلَىٰۚ قَالُواْ فَٱدۡعُواْۗ وَمَا دُعَـٰٓؤُاْ ٱلۡكَٰفِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَٰلٍ
(ዘበኞቹም) «መልእክተኞቻችሁ በተዓምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ፡፡ (ከሓዲዎቹም) «እንዴታ መጥተውናል እንጅ፤ (ግን አስተባበልናቸው)» ይላሉ፡፡ «እንግዲያውስ ጸልዩ፡፡ የከሓዲዎችም ጸሎት በከንቱ እንጅ አይደለም» ይሏቸዋል፡፡