فَإِنۡ أَعۡرَضُواْ فَقُلۡ أَنذَرۡتُكُمۡ صَٰعِقَةٗ مِّثۡلَ صَٰعِقَةِ عَادٖ وَثَمُودَ

(ከእምነት) እንቢ «ቢሉም እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የኾነን መቅሰፍት አስጠነቅቃችኋለሁ» በላቸው፡፡


إِذۡ جَآءَتۡهُمُ ٱلرُّسُلُ مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ قَالُواْ لَوۡ شَآءَ رَبُّنَا لَأَنزَلَ مَلَـٰٓئِكَةٗ فَإِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ

መልክተኞቹ አላህን እንጅ ሌላን አትግገዙ በማለት ከስተፊታቸውም ከስተኋለቸውም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር፡፡ ስለዚህ እኛ በዚያ በእርሱ በተላካችሁበት ከሓዲዎች ነን» አሉ፡፡


فَأَمَّا عَادٞ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَقَالُواْ مَنۡ أَشَدُّ مِنَّا قُوَّةًۖ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَهُمۡ هُوَ أَشَدُّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗۖ وَكَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ

ዓድም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ «ከእኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱ ማን ነው?» አሉም፡፡ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መኾኑን አያዩምን? በተዓምራታችንም ይክዱ ነበሩ፡፡


فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا صَرۡصَرٗا فِيٓ أَيَّامٖ نَّحِسَاتٖ لِّنُذِيقَهُمۡ عَذَابَ ٱلۡخِزۡيِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَخۡزَىٰۖ وَهُمۡ لَا يُنصَرُونَ

በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸውም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻን ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በኾኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው፡፡ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው፡፡ እነርሱም አይረዱም፡፡


وَأَمَّا ثَمُودُ فَهَدَيۡنَٰهُمۡ فَٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡعَمَىٰ عَلَى ٱلۡهُدَىٰ فَأَخَذَتۡهُمۡ صَٰعِقَةُ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡهُونِ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

ሰሙዶችማ መራናቸው ዕውርነትንም በቅንነት ላይ መረጡ፡፡ ይሠሩትም በነበሩት ኃጢኣት አሳናሽ የኾነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው፡፡



الصفحة التالية
Icon