وَلَئِنۡ أَذَقۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنَّا مِنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُ لَيَقُولَنَّ هَٰذَا لِي وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّجِعۡتُ إِلَىٰ رَبِّيٓ إِنَّ لِي عِندَهُۥ لَلۡحُسۡنَىٰۚ فَلَنُنَبِّئَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِمَا عَمِلُواْ وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ

ካገኘችውም መከራ በኋላ ከእኛ የኾነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ (በሥራዬ የተገባኝ) ነው፡፡ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብዬ አላስብም፡፡ ወደ ጌታየም ብመለስ ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ (ገነት) በእርግጥ አለችኝ» ይላል፡፡ እነዚያንም የካዱትን ሥራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን፡፡ ከብርቱውም ስቃይ በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን፡፡


وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ فَذُو دُعَآءٍ عَرِيضٖ

በሰውም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ (ከማመስገን) ይዞራል፡፡ በጎኑም ይርቃል፡፡ መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይኾናል፡፡


قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كَانَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ثُمَّ كَفَرۡتُم بِهِۦ مَنۡ أَضَلُّ مِمَّنۡ هُوَ فِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ

በላቸው «ንገሩኝ (ቁርኣኑ) ከአላህ ዘንድ ቢኾን ከዚያም በእርሱ ብትክዱ (ከውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከኾነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»


سَنُرِيهِمۡ ءَايَٰتِنَا فِي ٱلۡأٓفَاقِ وَفِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّۗ أَوَلَمۡ يَكۡفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ

እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?



الصفحة التالية
Icon