لِّلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ يَهَبُ لِمَن يَشَآءُ إِنَٰثٗا وَيَهَبُ لِمَن يَشَآءُ ٱلذُّكُورَ

የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡


أَوۡ يُزَوِّجُهُمۡ ذُكۡرَانٗا وَإِنَٰثٗاۖ وَيَجۡعَلُ مَن يَشَآءُ عَقِيمًاۚ إِنَّهُۥ عَلِيمٞ قَدِيرٞ

ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና፡፡


۞وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحۡيًا أَوۡ مِن وَرَآيِٕ حِجَابٍ أَوۡ يُرۡسِلَ رَسُولٗا فَيُوحِيَ بِإِذۡنِهِۦ مَا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ عَلِيٌّ حَكِيمٞ

ለሰውም አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን (መልአክን) የሚልክና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ (በገሃድ) ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡


وَكَذَٰلِكَ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ رُوحٗا مِّنۡ أَمۡرِنَاۚ مَا كُنتَ تَدۡرِي مَا ٱلۡكِتَٰبُ وَلَا ٱلۡإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلۡنَٰهُ نُورٗا نَّهۡدِي بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنۡ عِبَادِنَاۚ وَإِنَّكَ لَتَهۡدِيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡


صِرَٰطِ ٱللَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِلَى ٱللَّهِ تَصِيرُ ٱلۡأُمُورُ

ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡



الصفحة التالية
Icon