وَقَالُواْ مَا هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا يُهۡلِكُنَآ إِلَّا ٱلدَّهۡرُۚ وَمَا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَظُنُّونَ

እርሷም (ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ «እንሞታለን፤ ሕያውም እንኾናለን፡፡ ከጊዜም (ማለፍ) በስተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ፡፡ ለእነርሱም በዚህ (በሚሉት) ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡


وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱئۡتُواْ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡


قُلِ ٱللَّهُ يُحۡيِيكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يَجۡمَعُكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ

«አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ይገድላችኋል፣ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፡፡ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡


وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٖ يَخۡسَرُ ٱلۡمُبۡطِلُونَ

የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ፡፡


وَتَرَىٰ كُلَّ أُمَّةٖ جَاثِيَةٗۚ كُلُّ أُمَّةٖ تُدۡعَىٰٓ إِلَىٰ كِتَٰبِهَا ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

ሕዝብንም ሁሉ ተንበርካኪ ኾና ታያታለህ፡፡ ሕዝብ ሁሉ ወደ መጽሐፏ ትጥጠራለች፡፡ «ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ» (ይባላሉ)፡፡



الصفحة التالية
Icon