سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ለአላህ አሞገሰ፡፡ እርሱም ሁሉን አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡


لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡


هُوَ ٱلۡأَوَّلُ وَٱلۡأٓخِرُ وَٱلظَّـٰهِرُ وَٱلۡبَاطِنُۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ

እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡


هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۖ وَهُوَ مَعَكُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡


لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ

የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ነገሮችም (ሁሉ) ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡


يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۚ وَهُوَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል፡፡ እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ዐዋቂ ነወ፡፡



الصفحة التالية
Icon