أَءُنزِلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ مِنۢ بَيۡنِنَاۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّن ذِكۡرِيۚ بَل لَّمَّا يَذُوقُواْ عَذَابِ
«ከመካከላችን በእርሱ ላይ ቁርኣን ተወረደን?» (አሉ)፡፡ በእውነት እነርሱ ከግሳጼዬ (ከቁርኣን) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡
أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَحۡمَةِ رَبِّكَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡوَهَّابِ
ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?
أَمۡ لَهُم مُّلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ فَلۡيَرۡتَقُواْ فِي ٱلۡأَسۡبَٰبِ
ወይስ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የእነርሱ ነውን? (ነው ቢሉ) በመሰላሎችም ይውጡ፡፡
جُندٞ مَّا هُنَالِكَ مَهۡزُومٞ مِّنَ ٱلۡأَحۡزَابِ
እዚያ ዘንድ ከአሕዛብ የሆኑ ተሸናፊ ሰራዊት ናቸው፡፡
كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ ذُو ٱلۡأَوۡتَادِ
ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድም፣ የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባበሉ፡፡
وَثَمُودُ وَقَوۡمُ لُوطٖ وَأَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِۚ أُوْلَـٰٓئِكَ ٱلۡأَحۡزَابُ
ሰሙድም፣ የሉጥ ሰዎችም፣ የአይከት ሰዎችም (አስተባበሉ)፡፡ እነዚህ አሕዛቦቹ ናቸው፡፡
إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ
ሁሉም መልክተኞቹን ያስዋሹ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ ቅጣቴም ተረጋገጠባቸው፡፡
وَمَا يَنظُرُ هَـٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ مَّا لَهَا مِن فَوَاقٖ
እነዚህም ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲትን ጩኸት እንጅ ሌላን አይጠባበቁም፡፡