Surah Al-Ma'arij in አማርኛ
سورة المعارج · Verses: 44 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابࣲ وَاقِعࣲ
ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ -
2
لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعࣱ
በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ -
3
مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ
የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ -
4
تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمࣲ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةࣲ
መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ -
5
فَٱصۡبِرۡ صَبۡرࣰا جَمِيلًا
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ -
6
إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدࣰا
እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ -
7
وَنَرَىٰهُ قَرِيبࣰا
እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ -
8
يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ
ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ -
9
وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ
ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ -
10
وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمࣰا
ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ -
11
يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ
(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ -
12
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ
በሚስቱም በወንድሙም፡፡ -
13
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ
በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ -
14
وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعࣰا ثُمَّ يُنجِيهِ
በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ -
15
كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ -
16
نَزَّاعَةࣰ لِّلشَّوَىٰ
የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ -
17
تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ
(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ -
18
وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ
ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ -
19
۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا
ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ -
20
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعࣰا
ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ -
21
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا
መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ -
22
إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ
ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ -
23
ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ
እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ -
24
وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقࣱّ مَّعۡلُومࣱ
እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ -
25
لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ -
26
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ -
27
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ
እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ -
28
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونࣲ
የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ -
29
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ
እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ -
30
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ
በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ -
31
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ
ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ -
32
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ
እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ -
33
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ
እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ -
34
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ -
35
أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتࣲ مُّكۡرَمُونَ
እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ -
36
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ
ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? -
37
عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ
ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ -
38
أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيࣲٕ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمࣲ
ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? -
39
كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ
ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ -
40
فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ
በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ -
41
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرࣰا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ
ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ -
42
فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ
ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ -
43
يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعࣰا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبࣲ يُوفِضُونَ
ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ -
44
خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةࣱۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ
ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡