Surah An-Naba' in አማርኛ
سورة النبأ · Verses: 40 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ
ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? -
2
عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ
ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ -
3
ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ
ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ -
4
كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ
ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ -
5
ثُمَّ كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ
ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ -
6
أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدࣰا
ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን? -
7
وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادࣰا
ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን? -
8
وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجࣰا
ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ -
9
وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتࣰا
እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ -
10
وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسࣰا
ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ -
11
وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشࣰا
ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ -
12
وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعࣰا شِدَادࣰا
ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ -
13
وَجَعَلۡنَا سِرَاجࣰا وَهَّاجࣰا
አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ -
14
وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءࣰ ثَجَّاجࣰا
ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ -
15
لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبࣰّا وَنَبَاتࣰا
በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ -
16
وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا
የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ -
17
إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتࣰا
የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ -
18
يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجࣰا
በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ -
19
وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبࣰا
ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ -
20
وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا
ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ -
21
إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادࣰا
ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ -
22
لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابࣰا
ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ -
23
لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابࣰا
በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ -
24
لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدࣰا وَلَا شَرَابًا
በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ -
25
إِلَّا حَمِيمࣰا وَغَسَّاقࣰا
ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ -
26
جَزَآءࣰ وِفَاقًا
ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ -
27
إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابࣰا
እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ -
28
وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابࣰا
በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ -
29
وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبࣰا
ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ -
30
فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا
ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ -
31
إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا
ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ -
32
حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبࣰا
አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ -
33
وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابࣰا
እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ -
34
وَكَأۡسࣰا دِهَاقࣰا
የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ -
35
لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوࣰا وَلَا كِذَّٰبࣰا
በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ -
36
جَزَآءࣰ مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابࣰا
ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ -
37
رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابࣰا
የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ -
38
يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفࣰّاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابࣰا
መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ -
39
ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا
ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ -
40
إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابࣰا قَرِيبࣰا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا
እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡