ترجمة معاني سورة التكاثر باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation . ﰡ ﮣﮤ ﰀ በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ ﮦﮧﮨ ﰁ መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡ ﮪﮫﮬ ﰂ ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡ ﮮﮯﮰﮱ ﰃ ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ ﯔﯕﯖﯗﯘ ﰄ በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡ ﯚﯛ ﰅ ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡ ﯝﯞﯟﯠ ﰆ ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡ ﯢﯣﯤﯥﯦ ﰇ ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡