ترجمة سورة المطفّفين

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة المطفّفين باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡

ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡

ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡

እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?

በታላቁ ቀን፡፡

ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡

በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡

ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡

ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡

ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡

በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡

አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡

ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡

ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡

ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡

ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡

በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡

ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?

የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡

ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡

እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡

በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡

በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡

ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡

ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡

መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡

ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡

እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡

በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡

ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡

ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡

በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡

ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡

በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡

ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡
Icon