Surah Al-Buruj in አማርኛ
سورة البروج · Verses: 22 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡبُرُوجِ
የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ -
2
وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡمَوۡعُودِ
በተቀጠረው ቀንም፤ -
3
وَشَاهِدࣲ وَمَشۡهُودࣲ
በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ -
4
قُتِلَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأُخۡدُودِ
የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ -
5
ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلۡوَقُودِ
የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ -
6
إِذۡ هُمۡ عَلَيۡهَا قُعُودࣱ
እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ -
7
وَهُمۡ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ شُهُودࣱ
እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ -
8
وَمَا نَقَمُواْ مِنۡهُمۡ إِلَّآ أَن يُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ
ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ -
9
ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءࣲ شَهِيدٌ
በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ -
10
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُواْ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَتُوبُواْ فَلَهُمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمۡ عَذَابُ ٱلۡحَرِيقِ
እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ -
11
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتࣱ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡكَبِيرُ
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ -
12
إِنَّ بَطۡشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ
የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ -
13
إِنَّهُۥ هُوَ يُبۡدِئُ وَيُعِيدُ
እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ -
14
وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلۡوَدُودُ
እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ -
15
ذُو ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡمَجِيدُ
የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ -
16
فَعَّالࣱ لِّمَا يُرِيدُ
የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ -
17
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡجُنُودِ
የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን? -
18
فِرۡعَوۡنَ وَثَمُودَ
የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ -
19
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي تَكۡذِيبࣲ
በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ -
20
وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطُۢ
አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ -
21
بَلۡ هُوَ قُرۡءَانࣱ مَّجِيدࣱ
ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ -
22
فِي لَوۡحࣲ مَّحۡفُوظِۭ
የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡