Surah Ad-Duha in አማርኛ
سورة الضحى · Verses: 11 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
وَٱلضُّحَىٰ
በረፋዱ እምላለሁ፡፡ -
2
وَٱلَّيۡلِ إِذَا سَجَىٰ
በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤ -
3
مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَىٰ
ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡ -
4
وَلَلۡأٓخِرَةُ خَيۡرࣱ لَّكَ مِنَ ٱلۡأُولَىٰ
መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡ -
5
وَلَسَوۡفَ يُعۡطِيكَ رَبُّكَ فَتَرۡضَىٰٓ
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ -
6
أَلَمۡ يَجِدۡكَ يَتِيمࣰا فَـَٔاوَىٰ
የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡ -
7
وَوَجَدَكَ ضَآلࣰّا فَهَدَىٰ
የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡ -
8
وَوَجَدَكَ عَآئِلࣰا فَأَغۡنَىٰ
ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡ -
9
فَأَمَّا ٱلۡيَتِيمَ فَلَا تَقۡهَرۡ
የቲምንማ አትጨቁን፡፡ -
10
وَأَمَّا ٱلسَّآئِلَ فَلَا تَنۡهَرۡ
ለማኝንም አትገላምጥ፡፡ -
11
وَأَمَّا بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثۡ
በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡