Surah Al-Lail in አማርኛ
سورة الليل · Verses: 21 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰ
በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ -
2
وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ
በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡ -
3
وَمَا خَلَقَ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ
ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡ -
4
إِنَّ سَعۡيَكُمۡ لَشَتَّىٰ
ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡ -
5
فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ
የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡ -
6
وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ
በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ -
7
فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡيُسۡرَىٰ
ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ -
8
وَأَمَّا مَنۢ بَخِلَ وَٱسۡتَغۡنَىٰ
የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤ -
9
وَكَذَّبَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ
በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤ -
10
فَسَنُيَسِّرُهُۥ لِلۡعُسۡرَىٰ
ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ -
11
وَمَا يُغۡنِي عَنۡهُ مَالُهُۥٓ إِذَا تَرَدَّىٰٓ
በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ -
12
إِنَّ عَلَيۡنَا لَلۡهُدَىٰ
ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡ -
13
وَإِنَّ لَنَا لَلۡأٓخِرَةَ وَٱلۡأُولَىٰ
መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡ -
14
فَأَنذَرۡتُكُمۡ نَارࣰا تَلَظَّىٰ
የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡ -
15
لَا يَصۡلَىٰهَآ إِلَّا ٱلۡأَشۡقَى
ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡ -
16
ٱلَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡ -
17
وَسَيُجَنَّبُهَا ٱلۡأَتۡقَى
አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡ -
18
ٱلَّذِي يُؤۡتِي مَالَهُۥ يَتَزَكَّىٰ
ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡ -
19
وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُۥ مِن نِّعۡمَةࣲ تُجۡزَىٰٓ
ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ -
20
إِلَّا ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ رَبِّهِ ٱلۡأَعۡلَىٰ
ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ -
21
وَلَسَوۡفَ يَرۡضَىٰ
ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡