Surah Ash-Shams in አማርኛ
سورة الشمس · Verses: 15 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
وَٱلشَّمۡسِ وَضُحَىٰهَا
በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ -
2
وَٱلۡقَمَرِ إِذَا تَلَىٰهَا
በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤ -
3
وَٱلنَّهَارِ إِذَا جَلَّىٰهَا
በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤ -
4
وَٱلَّيۡلِ إِذَا يَغۡشَىٰهَا
በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤ -
5
وَٱلسَّمَآءِ وَمَا بَنَىٰهَا
በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤ -
6
وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا طَحَىٰهَا
በምድሪቱም በዘረጋትም፤ -
7
وَنَفۡسࣲ وَمَا سَوَّىٰهَا
በነፍስም ባስተካከላትም፤ -
8
فَأَلۡهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقۡوَىٰهَا
አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡ -
9
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن زَكَّىٰهَا
(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ -
10
وَقَدۡ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا
(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ -
11
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ بِطَغۡوَىٰهَآ
ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡ -
12
إِذِ ٱنۢبَعَثَ أَشۡقَىٰهَا
ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡ -
13
فَقَالَ لَهُمۡ رَسُولُ ٱللَّهِ نَاقَةَ ٱللَّهِ وَسُقۡيَٰهَا
ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡ -
14
فَكَذَّبُوهُ فَعَقَرُوهَا فَدَمۡدَمَ عَلَيۡهِمۡ رَبُّهُم بِذَنۢبِهِمۡ فَسَوَّىٰهَا
አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡ -
15
وَلَا يَخَافُ عُقۡبَٰهَا
ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡