Surah Al-Balad in አማርኛ
سورة البلد · Verses: 20 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ
በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ -
2
وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ
አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ -
3
وَوَالِدࣲ وَمَا وَلَدَ
በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ -
4
لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ
ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ -
5
أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدࣱ
በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? -
6
يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالࣰا لُّبَدًا
«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ -
7
أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ
አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? -
8
أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ
ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? -
9
وَلِسَانࣰا وَشَفَتَيۡنِ
ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ -
10
وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ
ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? -
11
فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ
ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ -
12
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ
ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? -
13
فَكُّ رَقَبَةٍ
(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ -
14
أَوۡ إِطۡعَٰمࣱ فِي يَوۡمࣲ ذِي مَسۡغَبَةࣲ
ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ -
15
يَتِيمࣰا ذَا مَقۡرَبَةٍ
የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ -
16
أَوۡ مِسۡكِينࣰا ذَا مَتۡرَبَةࣲ
ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ -
17
ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ
(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ -
18
أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ
እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ -
19
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ
እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ -
20
عَلَيۡهِمۡ نَارࣱ مُّؤۡصَدَةُۢ
በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡