Surah Al-Infitar in አማርኛ
سورة الإنفطار · Verses: 19 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنفَطَرَتۡ
ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ -
2
وَإِذَا ٱلۡكَوَاكِبُ ٱنتَثَرَتۡ
ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ -
3
وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ فُجِّرَتۡ
ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ -
4
وَإِذَا ٱلۡقُبُورُ بُعۡثِرَتۡ
መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ -
5
عَلِمَتۡ نَفۡسࣱ مَّا قَدَّمَتۡ وَأَخَّرَتۡ
ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ -
6
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ ٱلۡكَرِيمِ
አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? -
7
ٱلَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّىٰكَ فَعَدَلَكَ
በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ -
8
فِيٓ أَيِّ صُورَةࣲ مَّا شَآءَ رَكَّبَكَ
በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ -
9
كَلَّا بَلۡ تُكَذِّبُونَ بِٱلدِّينِ
ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ -
10
وَإِنَّ عَلَيۡكُمۡ لَحَٰفِظِينَ
በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ -
11
كِرَامࣰا كَٰتِبِينَ
የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ -
12
يَعۡلَمُونَ مَا تَفۡعَلُونَ
የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ -
13
إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمࣲ
እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ -
14
وَإِنَّ ٱلۡفُجَّارَ لَفِي جَحِيمࣲ
ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ -
15
يَصۡلَوۡنَهَا يَوۡمَ ٱلدِّينِ
በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ -
16
وَمَا هُمۡ عَنۡهَا بِغَآئِبِينَ
እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ -
17
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? -
18
ثُمَّ مَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? -
19
يَوۡمَ لَا تَمۡلِكُ نَفۡسࣱ لِّنَفۡسࣲ شَيۡـࣰٔاۖ وَٱلۡأَمۡرُ يَوۡمَئِذࣲ لِّلَّهِ
(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡