Surah Al-Mutaffifin in አማርኛ
سورة المطففين · Verses: 36 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
وَيۡلࣱ لِّلۡمُطَفِّفِينَ
ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡ -
2
ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ
ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡ -
3
وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ
ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ -
4
أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ
እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን? -
5
لِيَوۡمٍ عَظِيمࣲ
በታላቁ ቀን፡፡ -
6
يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡ -
7
كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينࣲ
በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡ -
8
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينࣱ
ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? -
9
كِتَٰبࣱ مَّرۡقُومࣱ
የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ -
10
وَيۡلࣱ يَوۡمَئِذࣲ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ -
11
ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡ -
12
وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ
በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡ -
13
إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ -
14
كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡ -
15
كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذࣲ لَّمَحۡجُوبُونَ
ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡ -
16
ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ
ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡ -
17
ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡ -
18
كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ
በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡ -
19
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ
ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? -
20
كِتَٰبࣱ مَّرۡقُومࣱ
የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ -
21
يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ
ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡ -
22
إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ -
23
عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ
በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡ -
24
تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ
በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡ -
25
يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقࣲ مَّخۡتُومٍ
ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ -
26
خِتَٰمُهُۥ مِسۡكࣱۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ
ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡ -
27
وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ
መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡ -
28
عَيۡنࣰا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ
ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ -
29
إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ
እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡ -
30
وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ
በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡ -
31
وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ
ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡ -
32
وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ
ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡ -
33
وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ
በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡ -
34
فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ
ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡ -
35
عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ
በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡ -
36
هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡