ترجمة معاني سورة الفيل باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation . ﰡ ﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓ ﰀ በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? ﮕﮖﮗﮘﮙ ﰁ ተንኮላቸውን በጥፋት ውስጥ (ከንቱ) አላደረገምን? (አድርጓል)፡፡ ﮛﮜﮝﮞ ﰂ በእነርሱም ላይ መንጎች የኾኑን ዎፎች ላከ፡፡ ﮠﮡﮢﮣ ﰃ ከተጠበሰ ጭቃ በኾነ ድንጋይ የምትወረውርባቸው የኾነችን፤ (አዕዋፍ)፡፡ ﮥﮦﮧ ﰄ ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራም አደረጋቸው፡፡