Surah Al-A'la in አማርኛ
سورة الأعلى · Verses: 19 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
سَبِّحِ ٱسۡمَ رَبِّكَ ٱلۡأَعۡلَى
ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ -
2
ٱلَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ
የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ -
3
وَٱلَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ
የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ -
4
وَٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلۡمَرۡعَىٰ
የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ -
5
فَجَعَلَهُۥ غُثَآءً أَحۡوَىٰ
(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ -
6
سَنُقۡرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰٓ
(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ -
7
إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ وَمَا يَخۡفَىٰ
አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ -
8
وَنُيَسِّرُكَ لِلۡيُسۡرَىٰ
ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ -
9
فَذَكِّرۡ إِن نَّفَعَتِ ٱلذِّكۡرَىٰ
ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ -
10
سَيَذَّكَّرُ مَن يَخۡشَىٰ
(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ -
11
وَيَتَجَنَّبُهَا ٱلۡأَشۡقَى
መናጢውም ይርቃታል፡፡ -
12
ٱلَّذِي يَصۡلَى ٱلنَّارَ ٱلۡكُبۡرَىٰ
ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ -
13
ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ
ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ -
14
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ
የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ -
15
وَذَكَرَ ٱسۡمَ رَبِّهِۦ فَصَلَّىٰ
የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ -
16
بَلۡ تُؤۡثِرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا
ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ -
17
وَٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرࣱ وَأَبۡقَىٰٓ
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ -
18
إِنَّ هَٰذَا لَفِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ
ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ -
19
صُحُفِ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ
በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡