Surah 'Abasa in አማርኛ
سورة عبس · Verses: 42 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ
ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ -
2
أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ
ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ -
3
وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ
ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ -
4
أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ
ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ -
5
أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ
የተብቃቃው ሰውማ፤ -
6
فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ
አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ -
7
وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ
ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ -
8
وَأَمَّا مَن جَآءَكَ يَسۡعَىٰ
እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ -
9
وَهُوَ يَخۡشَىٰ
እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ -
10
فَأَنتَ عَنۡهُ تَلَهَّىٰ
አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ -
11
كَلَّآ إِنَّهَا تَذۡكِرَةࣱ
ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ -
12
فَمَن شَآءَ ذَكَرَهُۥ
የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ -
13
فِي صُحُفࣲ مُّكَرَّمَةࣲ
በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ -
14
مَّرۡفُوعَةࣲ مُّطَهَّرَةِۭ
ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ -
15
بِأَيۡدِي سَفَرَةࣲ
በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ -
16
كِرَامِۭ بَرَرَةࣲ
የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ -
17
قُتِلَ ٱلۡإِنسَٰنُ مَآ أَكۡفَرَهُۥ
ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው? -
18
مِنۡ أَيِّ شَيۡءٍ خَلَقَهُۥ
(ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) -
19
مِن نُّطۡفَةٍ خَلَقَهُۥ فَقَدَّرَهُۥ
ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ -
20
ثُمَّ ٱلسَّبِيلَ يَسَّرَهُۥ
ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ -
21
ثُمَّ أَمَاتَهُۥ فَأَقۡبَرَهُۥ
ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ -
22
ثُمَّ إِذَا شَآءَ أَنشَرَهُۥ
ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ -
23
كَلَّا لَمَّا يَقۡضِ مَآ أَمَرَهُۥ
በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ -
24
فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ إِلَىٰ طَعَامِهِۦٓ
ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ -
25
أَنَّا صَبَبۡنَا ٱلۡمَآءَ صَبࣰّا
እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ -
26
ثُمَّ شَقَقۡنَا ٱلۡأَرۡضَ شَقࣰّا
ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ -
27
فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا حَبࣰّا
በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ -
28
وَعِنَبࣰا وَقَضۡبࣰا
ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ -
29
وَزَيۡتُونࣰا وَنَخۡلࣰا
የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ -
30
وَحَدَآئِقَ غُلۡبࣰا
ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ -
31
وَفَٰكِهَةࣰ وَأَبࣰّا
ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ -
32
مَّتَٰعࣰا لَّكُمۡ وَلِأَنۡعَٰمِكُمۡ
ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ -
33
فَإِذَا جَآءَتِ ٱلصَّآخَّةُ
አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ -
34
يَوۡمَ يَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِيهِ
ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ -
35
وَأُمِّهِۦ وَأَبِيهِ
ከናቱም ካባቱም፤ -
36
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَبَنِيهِ
ከሚስቱም ከልጁም፤ -
37
لِكُلِّ ٱمۡرِيࣲٕ مِّنۡهُمۡ يَوۡمَئِذࣲ شَأۡنࣱ يُغۡنِيهِ
ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ -
38
وُجُوهࣱ يَوۡمَئِذࣲ مُّسۡفِرَةࣱ
ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ -
39
ضَاحِكَةࣱ مُّسۡتَبۡشِرَةࣱ
ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ -
40
وَوُجُوهࣱ يَوۡمَئِذٍ عَلَيۡهَا غَبَرَةࣱ
ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ -
41
تَرۡهَقُهَا قَتَرَةٌ
ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ -
42
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَفَرَةُ ٱلۡفَجَرَةُ
እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡