Surah Al-'Alaq in አማርኛ
سورة العلق · Verses: 19 · Meccan
Translation: አማርኛ translation 1 (الترجمة الأمهرية)
-
1
ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ
አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ -
2
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ
ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ -
3
ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ
አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ -
4
ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ
ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ -
5
عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ
ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ -
6
كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ
በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ -
7
أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ
ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ -
8
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ
መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ -
9
أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ
አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ -
10
عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ
ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ -
11
أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ
አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ -
12
أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ
ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ -
13
أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ
አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ -
14
أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ
አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? -
15
كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ
ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ -
16
نَاصِيَةࣲ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةࣲ
ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ -
17
فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ
ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ -
18
سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ
(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ -
19
كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡