ترجمة معاني سورة الطلاق باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation
ﰡ
آية رقم 1
አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ግልጽ የኾነችን ጠያፍ ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ አይውጡም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፡፡ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡
آية رقم 2
ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡
آية رقم 3
ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡
آية رقم 4
እኒያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸው ሕግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው)፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡
آية رقم 5
ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደእናንተ አወረደው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርይለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡
آية رقم 6
ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ቢኾኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ፡፡ ለእናንተም (ልጆቻችሁን) ቢያጠቡላችሁ ምንዳዎቻቸውን ስጧቸው፡፡ በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፡፡ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች፡፡
آية رقم 7
የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፡፡ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይቀልብ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድድም፡፡ አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል፡፡
آية رقم 8
ከከተማም ከጌታዋ ትዕዛዝ ከመልክተኞቹም ያመጸች፣ ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት፣ መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት፡፡
آية رقم 9
የነገርዋንም ቅጣት ቀመሰች፡፡ የነገርዋም መጨረሻ ከሳራ ኾነ፡፡
آية رقم 10
አላህ ለእነርሱ ብርቱን ቅጣት አዘጋጀ፡፡ እናንተም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ እነዚያ ያመኑ (ሆይ)! አላህ ወደናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፡፡ መልክተኛን (ላከ)፡፡
آية رقم 11
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን (ላከ)፡፡ በአላህም አንቀጾች የሚያምን፣ መልካምን ሥራ የሚሠራም ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፡፡ አላህ ለእርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ፡፡
آية رقم 12
አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በዕውቀት ያካበበ መኾኑን በዕውቀት ያካበበ መኾኑን ታወቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)፡፡
تقدم القراءة