ترجمة سورة العاديات

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة العاديات باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡

(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤

በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤

በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤

በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡

ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡

እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡

(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤

በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡

ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡
Icon