ترجمة سورة لقمان

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة لقمان باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

አ.ለ.መ. (አሊፍ ላም ሚም)፡፡
ይህች ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡
ለበጎ አድራጊዎች መሪና እዝነት ስትኾን፡፡
ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚያደርሱት፣ ዘካንም ለሚሰጡት፣ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት፡፡
እነዚያ ከጌታቸው በሆነ ቅን መንገድ ላይ ናቸው፡፡ እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡
ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡
አንቀጾቻችንም በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል፡፡ በአሳማሚ ቅጣትም አብስረው፡፡
እነዚያ ያመኑና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው፡፡
በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ፤ አላህም እውነተኛን ተስፋ ቃል ገባላቸው፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡
ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡
ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልነውም)፡- «አላህን አመስግን፡፡» ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የካደም ሰው (በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና፡፡
ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡
ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም
ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)፡፡
(ሉቅማንም አለ) «ልጄ ሆይ! እርሷ የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል፡፡ አላህ ሩኅሩኅ ውስጥ ዐዋቂ ነውና፡፡
«ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፡፡ በበጎ ነገርም እዘዝ፡፡ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፡፡ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ ይህ በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው፡፡
«ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና፡፡
«በአካኼድህም መካከለኛ ኹን፡፡ ከድምጽህም ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና፡፡»
አላህ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን? ከሰዎችም ያለ ዕውቀትና ያለ መሪ፣ ያለግልጽ መጽሐፍም በአላህ የሚከራከር አልለ፡፡
ለእነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን ይላሉ፡፡ ሰይጣን ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም (ይከተሉዋቸዋልን?)
እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡
የካደም ሰው ክህደቱ አያሳዝንህ፡፡ መመለሻቸው ወደኛ ነው፤ የሠሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን፡፡ አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡
ጥቂትን እናጣቅማቸዋለን፡፡ ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን፡፡
ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፡፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው በላቸው፡፡ ይልቁንም አብዛኛዎቹ አያውቁም፡፡
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡
ከዛፍም በምድር ያለው ሁሉ ብእሮች ቢሆኑ ኖሮ ባሕሩም ከእርሱ (ማለቅ) በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ (ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው) የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡
እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና፡፡
አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፣ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ መሆኑን አታይምን? ሁሉም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
ይህ አላህ እርሱ እውነት ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት (ጣዖት) ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው፡፡
ከአስደናቂ ምልክቶቹ ሊያሳያችሁ መርከቦች በአላህ ችሮታ በባህር ውስጥ የሚንሻለሉ መሆናቸውን አታይምን? በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ ተዓምራቶች አሉበት፡፡
እንደ ጥላዎችም የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስም ባዳናቸው ጊዜ ከእነሱ ትክክለኛም አልለ፡፡ (ከእነርሱም የሚክድ አለ)፡፡ በአንቀጾቻችንም አታላይ ከዳተኛ ሁሉ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡
እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ፡፡ በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ፡፡
አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ዝናብንም ያወርዳል፡፡ በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም ነገ የምትሠራውን አታውቅም፡፡ ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ አላህ ዐዋቂ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
Icon