ترجمة سورة التين

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة التين باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡

በሲኒን ተራራም፤

በዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡

ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡

ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡

ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡

ታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?

አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡
Icon