ترجمة سورة الفجر

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة الفجر باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

በጎህ እምላለሁ፡፡
በዐሥር ሌሊቶችም፡፡
በጥንዱም በነጠላውም፡፡
በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡
በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን?
ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን?
በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡
በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡
በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡
በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡
በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡
በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?)
በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡
ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡
ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡
በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡
ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡
ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡
የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡
ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡
ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤
መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ለሱ ክብር በምስማማ መልኩ) በመጣ ጊዜ፤
ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ?
«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡
በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡
የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡
(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!
«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡
«በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡
ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡
Icon