ترجمة معاني سورة القارعة باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation . ﰡ ﭴ ﰀ ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤ ﭶﭷ ﰁ ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት! ﭹﭺﭻﭼ ﰂ ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? ﭾﭿﮀﮁﮂ ﰃ ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤ ﮄﮅﮆﮇ ﰄ ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡) ﮉﮊﮋﮌ ﰅ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤ ﮎﮏﮐﮑ ﰆ እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡ ﮓﮔﮕﮖ ﰇ ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤ ﮘﮙ ﰈ መኖሪያው ሃዊያህ ናት ﮛﮜﮝﮞ ﰉ እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? ﮠﮡ ﰊ (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡