ترجمة سورة النّمل

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة النّمل باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

ጠ.ሰ (ጣ ሲን) ይህቺ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡
ለምእምናን መሪና ብስራት ናት፡፡
ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት ዘካንም ለሚሰጡት እነሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት፡፡
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነሱ (ክፉ) ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ፡፡
እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ለእነርሱ ያላቸው ናቸው፡፡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡
አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና ዐዋቂ ከኾነው (ጌታህ) ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ፡፡
ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፡፡ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ (የኾነውን አውሳላቸው)፡፡
በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፤ «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሁሉ ተባረኩ፡፡ የዐለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው፡፡»
«ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ፡፡
«በትርህንም ጣል» (ተባለ ጣለም)፡፡ እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ፤ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ፡፡ አልተመለሰምም፡፡ «ሙሳ ሆይ! አትፈራ፤ እኔ መልክተኞቹ እኔ ዘንድ አይፈሩምና፡፡
«ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ አዛኝ ነኝ፡፡
«እጅህንም በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፡፡ ያለነውር (ያለ ለምጽ) ነጭ ኾና ትወጣለችና፡፡ በዘጠኝ ተዓምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ (ኺድ)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸውና፡፡
ተዓምራታችንም ግልጽ ኾና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ፡፡ የአመጸኞችም ፍጻሜ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡
ለዳውድና ለሱለይማንም ዕውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ አሉም፡- «ምስጋና ለአላህ ለእዚያ ከምእምናን ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን ይገባው፡፡»
ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፡፡ አለም «ሰዎች ሆይ! የበራሪን ንግግር (የወፍን ቋንቋ) ተስተማርን፡፡ ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን፡፡ ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የኾነ ችሮታ ነው፡፡»
ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጋኔን፣ ከሰውም፣ ከበራሪም የኾኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም ይከመከማሉ፡፡
በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ
ከንግግርዋም እየሳቀ ጥርሱን ፈገግ አደረገ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ» አለ፡፡
በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም «ሁድሁድን ለምን አላየውም! በእውነቱ ከራቁት ነበርን፡፡
«ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ ዐርደዋለሁ፤ ወይም ግልጽ በኾነ አስረጅ ይመጣኛል» (አለ)
(ወፉ) ዕሩቅ ያልኾነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም «ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡
«እኔ የምትገዛቸው የኾኑችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችኝ አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡
«እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል፡፡ ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም፡፡»
ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገ ልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)፡፡
አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው፡፡
(ሱለይማንም) አለ «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ኾንክ ወደፊት እናያለን፡፡
«ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ኺድ፡፡ ወደእነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ ምን አንደሚመልሱም ተመልከት፡፡»
(እርሷም በደረሳት ጊዜ) አለች «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደኔ ተጣለ፡፡
«እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
«በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ፤ (የሚል ነው)፡፡
«እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ (የሚበጀውን) ንገሩኝ፡፡ እስከምትገኙልኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች፡፡
«እኛ የኀይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን፡፡ ግን ትዕዛዙ ወደ አንቺ ነው፡፡ ምን እንደምታዢም አስተውዪ፤» አሏት፡፡
(እርሷም) አለች «ንጉሦች ከተማን (በኀይል) በገቡባት ጊዜ ያበላሹዋታል፡፡ የተከበሩ ሰዎችዋንም ወራዶች ያደርጋሉ፡፡ እንደዚሁም (እነዚህ) ይሠራሉ፡፡
«እኔም ወደእነርሱ ገጸ በረከትን የምልክና መልክተኞቹ በምን እንደሚመለሱ የምጠባበቅ ነኝ፡፡»
(መልክተኛው) ሱለይማንንም በመጣው ጊዜ አለ «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን አላህም የሰጠኝ ከሰጣችሁ የበለጠ ነው፡፡ ይልቁንም እናንተ በገጸ በረከታችሁ ትደሰታላችሁ፡፡»
«ወደእነሱ ተመለስ፡፡ ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን፡፡ ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ኾነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን» (አለ)፡፡
«እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ኾነው ሳይመጡኝ በፊት ዙፋንዋን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው» አለ፡፡
ከጋኔን ኀይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ፡፡ እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ» አለ፡፡
ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ዕውቀት ያለው ሰው (የተገለጸው) «ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ» አለ፤ (እንደዚሁም አደረገ)፡፡ እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየውም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው» አለ፡፡
«ዙፋንዋን ለእርሷ አሳስቱ፡፡ ታውቀው እንደኾነ ወይም ከእነዚያ ከማያወቁት ትኾን እንደሆነ፤ እናያለን፤» አላቸው፡፡
በመጣች ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን» ተባለች፡፡ «እርሱ ልክ እርሱ ነው መሰለኝ» አለች፡፡ (ሱለይማን) «ከእርሷ በፊትም ዕውቀትን ተሰጠን ሙስሊሞችም ነበርን፤» (አለ)፡፡
ከአላህ ሌላ ትግገዛው የነበረችውንም ከለከላት፡፡ እርሷ ከከሓዲዎች ሕዝቦች ነበረችና፡፡
ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡ «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ሕንጻ ነው» አላት፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ» አለች፡፡
ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊሕን አላህን ተገዙ በማለት በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም እነሱ የሚነታረኩ ሁለት ጭፍሮች ኾኑ፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! ከመልካሙ በፊት በክፉው (ቅጣትን አምጣብን በማለት) ለምን ታስቸኩላላችሀ ይታዘንላችሁ ዘንድ አላህን ምሕረትን አትለምኑምን» አላቸው፡፡
«ባንተና ከአንተም ጋር ባሉት ሰዎች ምክንያት ገደቢሶች ኾን» አሉት፡፡ «ገደቢስነታችሁ አላህ ዘንድ ነው፤ ይልቁንም እናንተ የምትፈተኑ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡
በከተማይቱም ውስጥ በምድር ውስጥ የሚያበላሹና የማያሳምሩ ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ፡፡
«እርሱንና ቤተሰቦቹን ሌሊት ልንገድል ከዚያም ለዘመዱ የቤተሰቦቹን ጥፋት (መገደላቸውን) አላየንም፤ እኛም እውነተኞች ነን ልንል በአላህ ተማማሉ» አሉ፡፡
ተንኮልንም መከሩ፡፡ እነርሱም የማያወቁ ሲኾኑ በተንኮላቸው አጠፋናቸው፡፡
የተንኮላቸውም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እኛ እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም በሙሉ እንዴት እንዳጠፋናቸው ተመልከት፡፡
እኚህም በበደላቸው ምክንያት ባዶዎች ሲሆኑ ቤቶቻቸው ናቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያወቁ ሕዝቦች አስደናቂ ተዓምር አለበት፡፡
እነዚያንም ያመኑትንና ከክሕደት ይጠነቀቁ የነበሩትን አዳን፡፡
ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ «እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን
«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡»
የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡
እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳን፡፡ ሚስቱ፤ ብቻ ስትቀር፡፡ (በጥፋቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ አደረግናት፡፡
በእነርሱም ላይ (የድንጋይ) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናብ ከፋ፡፡
(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡
ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡
ወይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ፣ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ፣ በሁለቱ ባሕሮችም (በጣፋጩና በጨው ባሕር) መካከል ግርዶን ያደረገ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡
ወይም ያ በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፋሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን አላህ (በእርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ፡፡
ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን «እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ አስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡
«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡
በእውነት የመጨረሻይቱን ዓለም (ኹኔታ) ማወቃቸው ተሟላን አይደለም እነርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእውነትም እነርሱ ከእርሷ ዕውሮች ናቸው፡፡
እነዚያም የካዱት አሉ «እኛም አባቶቻችንም ዐፈር በኾን ጊዜ እኛ (ከመቃብር) የምንወጣ ነን
«ይህንን እኛም ከፊት የነበሩት አባቶቻችንም በእርግጥ ተቀጥረንበታል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጅ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡
«በምድር ላይ ኺዱ፡፡ የአመጸኞችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡
በእነሱም ላይ አትዘን፡፡ ከሚመክሩብህም ነገር በጭንቀት ውስጥ አትኹን፡፡
«እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡
«የዚያ የምትቻኮሉበት ከፊሉ ለእናንተ የቀረበ መኾኑ ተረጋግጧል» በላቸው፡፡
ጌታህም በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያመሰግኑም፡፡
ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ያውቃል፡፡
በሰማይና በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ገላጭ በኾነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢኾን እንጅ፡፡
ይህ ቁርኣን በእስራኤል ልጆች ላይ የእነዚያን እነርሱ በእርሱ የሚለያዩበትን አብዛኛውን ይነግራል፡፡
እርሱም ለምእምናን መምሪያና እዝነት ነው፡፡
ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፡፡ እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው፡፡
በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ አንተ ግልጽ በኾነው እውነት ላይ ነህና፡፡
አንተ ሙታንን አታሰማም፡፡ ደንቆሮዎችንም የሚተው ኾነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም፡፡
አንተም (ልበ) ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም፡፡ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን በስተቀር አታሰማም፡፡ እነርሱ ፍጹም ታዛዦች ናቸውና፡፡
በእነርሱም ላይ (የቅጣት) ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአንቀጾቻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣለን፡፡
ከሕዝቦቹም ሁሉ ባንቀፆቻችን የሚያስተባብሉትን ጭፍሮች የምንሰበስብበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነሱም ይከመከማሉ፡፡
በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን ወይስ ምንን ትሠሩ ነበራችሁ»
በመበደላቸውም በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እነርሱም አይናገሩም፡፡
እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንዲያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ ተዓምራቶች አሉበት፡፡
በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ (የሚኾነውን አስታውስ)፡፡ ሁሉም የተናነሱ ኾነውም ወደርሱ ይመጣሉ፡፡
ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ (ተመልከት)፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርስዋ የበለጠ ምንዳ አልለው፡፡ እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ጸጥተኞች ናቸው፡፡
በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡
የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንድግገዛ ብቻ ነው፡፡ ነገሩንም ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ከሙስሊሞችም እንድኾን ታዝዣለሁ (በላቸው)፡፡
ቁርኣንንም እንዳነብ (ታዝዣለሁ)፡፡ የተመራም ሰው የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው «እኔ ከአስጠንቃቂዎች ነኝ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በለው፡፡
ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቋትምአላችሁ» በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
Icon