ترجمة سورة القصص

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة القصص باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

ጠ.ሰ.መ (ጣ ሲን ሚም)፡፡
ይህቺ ገላጭ ከሆነው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡
ከሙሳና ከፈርዖን ዜና እውነተኞች ስንኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች ባንተ ላይ እናነባለን፡፡
ፈርዖን በምድር ላይ ተንበጣረረ፡፡ ነዋሪዎቿንም የተከፋፈሉ ጓዶች አደረጋቸው፡፡ ከእነርሱ ጭፍሮችን ያዳክማል፡፡ ወንዶች ልጆቻቸውን በብዛት ያርዳል፡፡ ሴቶቻቸውንም ይተዋል፤ እርሱ ከሚያበላሹት ሰዎች ነበርና፡፡
በእነዚያም በምድር ውስጥ በተጨቆኑ ላይ ልንለግስ፣ መሪዎችም ልናደርጋቸው ወራሾችም ልናደርጋቸው እንሻለን፡፡
ለእነርሱም በምድር ላይ ልናስመች ፈርዖንንና ሃማንንም ሰራዊቶቻቸውንም ከእነሱ ይፈሩት የነበሩትን ነገር ልናሳያቸው (እንሻለን)፡፡
ወደ ሙሳም እናት «አጥቢው፣ በርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና» ማለትን አመለከትን፡፡
የፈርዖን ቤተሰቦችም (መጨረሻው) ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት፡፡ ፈርዖንና ሃማንም ሰራዊቶቻቸውም ሀጢአተኞች ነበሩ፡፡
የፈርዖንም ሚስት «ለእኔ የዓይኔ መርጊያ ነው፡፡ ለአንተም፡፡ አትግደሉት፡፡ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አለች፡፡ እነርሱም (ፍጻሜውን) የማያውቁ ሆነው (አነሱት)፡፡
የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ፡፡ ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር፡፡
ለእኅቱም ተከታተይው አለቻት፡፡ እርሱንም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፡፡
(ወደናቱ ከመመለሱ) በፊትም አጥቢዎችን (መጥባትን) በእርሱ ላይ እርም አደረግን፡፡ (እኅቱ) «ለእናንተ የሚያሳድጉላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን» አለችም፡፡
ወደእናቱም ዓይንዋ እንድትረጋ፣ እንዳታዝንም፣ የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ጊዜ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ፡፡ በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎችን አገኘ፡፡ ይህ ከወገኑ ነው፤ ይህም ከጠላቱ ነው፡፡ ያም ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጠላቱ በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው፡፡ ሙሳም በጡጫ መታው፡፡ ገደለውም፡፡ ይህ ከሰይጣን ሥራ ነው፡፡ እርሱ ግልጽ አሳሳች ጠላት ነውና አለ፡፡
«ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ለእኔም ማር አለ፡፡» ለእርሱም ምሕረት አደረገለት እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
«ጌታዬ ሆይ! በእኔ ላይ በመለገስህ ይሁንብኝ (ከስህተቴ እጸጸታለሁ)፤ ለአመጸኞችም ፈጽሞ ረዳት አልሆንም አለ፡፡
በከተማይቱም ውስጥ ፈሪ የሚጠባበቅ ሆኖ አደረ፡፡ በድንገትም ያ ትላንት እርዳታን የጠየቀው ሰው በጩኸት እርዳታን ይጠይቀዋል፡፡ ሙሳ ለርሱ «አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ» አለው፡፡
(ሙሳ) ያንን እርሱ ለሁለቱም ጠላት የሆነውን ሰው በኃይል ሊይዘው በፈለገም ጊዜ «ሙሳ
ከከተማይቱም ዳርቻ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ፡፡ «ሙሳ ሆይ! ሹማምንቶቹ ሊገድሉህ ባንተ ይመካከራሉና ውጣ፡፡ እኔ ላንተ ከመካሪዎች ነኝና» አለው፡፡
የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ከበደለኞቹ ሕዝቦች አድነኝ» አለ፡፡
ወደ መድየን አቅጣጫ ፊቱን ባዞረ ጊዜም «ጌታዬ ቀጥተኛውን መንገድ ሊመራኝ እከጅላለሁ» አለ፡፡
ወደ መድየንም ውሃ በመጣ ጊዜ በእርሱ ላይ ከሰዎች ጭፍሮችን (መንጋዎቻቸውን) የሚያጠጡ ሆነው አገኘ፡፡ ከእነርሱ በታችም (ከውሃው መንጎቻቸውን) የሚከለክሉን ሁለት ሴቶች አገኘ፡፡ «ነገራችሁ ምንድን ነው» አላቸው፡፡ «እረኞቹ ሁሉ (መንጋዎቻቸውን) እስከሚመልሱ አናጠጣም፡፡ አባታችንም ትልቅ ሽማግሌ ነው» አሉት፡፡
ለሁለቱም አጠጣላቸው፡፡ ከዚያም ወደ ጥላው ዘወር አለ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ» አለ፡፡
ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትኼድ ሆና መጣችው፡፡ «አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል» አለችው፡፡ ወደእርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ በተረከለትም ጊዜ «አትፍራ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ድነሃል» አለው፡፡
ከሁለቱ አንደኛይቱም «አባቴ ሆይ ቅጠረው፡፡ ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ ብርቱው ታማኙ ነውና» አለችው፡፡
«ስምንትን ዓመታት ልታገለግለኝ እኔ ከእነዚህ ሁለት ሴቶቸ ልጆቼ አንዲቱን ላጋባህ እሻለሁ፡፡ ዐስርን ብትሞላም ከአንተ ነው፡፡ ባንተ ላይ ማስቸገርንም አልሻም፡፡ አላህ የሻ እንደ ኾነ ከመልካሞቹ ሰዎች ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡
(ሙሳም) «ይህ (ውለታ) በእኔና ባንተ መካከል (ረጊ) ነው፡፡ ከሁለቱ ጊዜያቶች ማንኛውንም ብፈጽም በእኔ ላይ ወሰን ማለፍ የለም፡፡ አላህም በምንለነው ላይ ምስክር» ነው አለ፡፡
ሙሳም ጊዜውን በጨረሰና ከቤተሰቦቹ ጋር በኼደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ፡፡ ለቤተሰቡ (እዚህ) «ቆዩ፡፡ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ወሬን ወይም ትሞቁ ዘንድ ከእሳት ትንታግን አመጣላችኋለሁ» አለ፡፡
በመጣትም ጊዜ ከሸለቆው ቀኝ ዳርቻ ከዛፊቱ በኩል በተባረከችው ስፍራ ውስጥ «ሙሳ ሆይ! እኔ የዓለማት ጌታ አላህ እኔ ነኝ» በማለት ተጠራ፡፡
«በትርህንም ጣል» (ተባለ)፡፡ እንደ ትንሽ እባብ ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ወደ ኋላ ዞሮ ሸሸ፤ አልተመለሰምም፡፡ «ሙሳ ሆይ! ተመለስ አትፍራም፤ አንተ ከጥብቆቹ ነህና» (ተባለም)፡፡
«እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፡፡ ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፡፡ ክንፍህንም ከፍርሃት (ለመዳን) ወዳንተ አጣብቅ፡፡ እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንንቶቹ የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡»
(ሙሳ) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ፡፡ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡
«ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ ረዳት ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና፡፡»
(አላህም) «ጡንቻህን በወንድምህ በእርግጥ እናበረታለን፡፡ ለሁለታችሁም ስልጣንን እናደርጋለን፡፡ ወደእናንተም (በመጥፎ) አይደርሱም፡፡ በተዓምራቶቻችን (ኺዱ)፡፡ እናንተና የተከተላችሁም ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ» አላቸው፡፡
ሙሳም በታምራቶቻችን ግልጽ ኾነው በመጣባቸው ጊዜ «ይህ የተቀጠፈ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ይህንንም በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን ውስጥ አልሰማንም» አሉ፡፡
ሙሳም «ጌታዬ ከእርሱ ዘንድ በቀጥታው መንገድ የመጣውን ሰው ምስጉኒቱም አገር ለእርሱ የምትኾንለትን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እነሆ በደለኞቹ አይድኑም» አለ፡፡
ፈርዖንም «እናንተ ጭፍሮች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላወቅሁም፡፡ ሃማንም ሆይ! ጭቃን ለእኔ አቃጥልልኝ፤ (ጡብ ሥራልኝ)፡፡ ለእኔም ከፍተኛ ሕንጻን ሥራልኝ፡፡ ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና፡፡ እኔም ከውሸታሞቹ መኾኑን እጠረጥረዋለሁ» አለ፡፡
እርሱም ሰራዊቶቹም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፡፡ እነርሱም ወደእኛ የማይመለሱ መኾናቸውን ጠረጠሩ፡፡
እርሱንም ሰራዊቱንም በጥብቅ ያዝናቸው፡፡ በባሕርም ውስጥ ጣልናቸው፡፡ የበደለኞች መጨረሻም፤ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡
ወደ እሳት የሚጠሩ መሪዎችም አደረግናቸው፡፡ በትንሣኤም ቀን አይርረዱም፡፡
በይህችም በቅርቢቱም ዓለም ውስጥ እርግማንን አስከተልናቸው፡፡ በትንሣኤም ቀን እነሱ ከሚባረሩት ናቸው፡፡
የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦችም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲኾን ይገሰጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡
ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ (ከተራራው) በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም ከተጣዱትም አልነበርክም፡፡
ግን እኛ (ከእርሱ በኋላ) የክፍለ ዘመናትን ሰዎች አስገኘን፡፡ በእነሱም ላይ ዕድሜዎች ተራዘሙ፡፡ በመድየንም ሰዎች ውስጥ ተቀማጭ በእነሱ ላይ አንቀጾቻችን የምታነብ አልነበርክም፡፡ ግን እኛ ላኪዎችህ ኾንን፡፡
በጠራነውም ጊዜ በጡር ጎን አልነበርክም፡፡ ግን ከአንተ በፊት ምንም አስፈራሪ ያልመጣቸውን ሕዝቦች ታስፈራራ ዘንድ ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ላክንህ) ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡
እጆቻቸውም ባሳለፉት ምክንያት መከራ የምትነካቸውና «ጌታችን ሆይ! አንቀጾችህን እንድንከተል ከምእምናንም እንድንኾን ወደኛ መልክተኛን አትልክም ኖሯልን» የሚሉ ባልኾኑ ኖሮ (አንልክም ነበር)፡፡
እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ «ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይስሰጠውም ኖሯልን» አሉ፡፡ «ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን የተረዳዱ ሁለት ድግምቶች ናቸው» አሉ፡፡
«ከአላህ ዘንድ የኾነን መጽሐፍ እርሱ ከሁለቱም ይበልጥ ቅን የኾነን አምጡ፡፡ እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ብታመጡት) እከተለዋለሁ» በላቸው፡፡
እሺ ባይሉህም፤ የሚከተሉት፤ ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ አላህ በደለኞች ሕዝቦችን አይመራምና፡፡
ይገሰጹም ዘንድ ቃልን (ቁርኣንን በያይነቱ) ለእነርሱ በእርግጥ አስከታተልን፡፡
እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ ያምናሉ፡፡
በእነሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡
እነዚያ በመታገሳቸው ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይስሰጣሉ፡፡ ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ፡፡ ከሰጠናቸውም ሲሳይ ይለግሳሉ፡፡
ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ፡፡ «ለእኛ ሥራዎቻችን አሉን፡፡ ለናንተም ሥራዎቻችሁ አሏችሁ፡፡ ሰላም በእናንተ ላይ (ይኹን) ባለጌዎችን አንፈልግም» ይላሉ፡፡
አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡
«ከአንተ ጋር ቅንን መንገድ ብንከተል ከምድራችን እንባረራለን» አሉም፡፡ ከእኛ ዘንድ (የተሰጠ) ሲሳይ ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፍሬዎች ወደእርሱ የሚነዱበትን ጸጥተኛ ክልል (መካን) ለእነሱ አላስመቸናቸውምን ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
ከከተማም ኑሮዋን (ምቾቷን) የካደችን (ከተማ) ያጠፋናት ብዙ ናት፡፡ እነዚህም ከእነሱ በኋላ ጥቂት ጊዜ እንጅ ያልተኖረባቸው ሲኾኑ መኖሪያዎቻቸው ናቸው፡፡ እኛም (ከእነርሱ) ወራሾች ነበርን፡፡
ጌታህም ከተሞችን በዋናዋ (ከተማ) ውስጥ አንቀጾቻችንን በእነሱ ላይ የሚያነብ መልክተኛን እስከሚልክ ድረስ አጥፊ አልነበረም፡፡ ከተሞችንም ባለቤቶቿ በዳዮች ሆነው እንጅ አጥፊዎች አልነበርንም፡፡
ከማንኛውም ነገር የተሰጣችሁት፤ የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅምና ጌጧ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም (ምንዳ) በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው አታውቁምን
መልካምን ተስፋ ቃል የገባንለትና እርሱም አግኚው የሆነ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም እንዳስመቸነውና ከዚያም እርሱ በትንሣኤ ቀን (ለእሳት) ከሚቀረቡት እንደ ኾነው ሰው ነውን
(አላህ) የሚጠራባቸውንና እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
እነዚያ በእነርሱ ላይ ቃሉ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፡፡ እንደጠመምን አጠመምናቸው፡፡ (ከእነሱ) ወዳንተ ተጥራራን፡፡ እኛን ይግገዙ አልነበሩም፡፡
«(ለአላህ) የምታጋሯቸውንም ጥሩ» ይባላሉ፤ ይጠሯቸዋልም፡፡ ግን ለእነርሱ አይመልሱላቸውም፡፡ ቅጣቱንም ያያሉ፡፡ እነርሱ ይመሩ በነበሩ ኖሮ (አያዩትም ነበር)፡፡
«የሚጠራባቸውንና ለመልክተኞቹም ምንን መለሳችሁ» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
በዚያም ቀን ወሬዎቹ ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰውሩባቸዋል፡፡ እነርሱም አይጠያየቁም፡፡
የተጸጸተና ያመነ ሰውማ መልካምንም የሠራ ከሚድኑት ሊኾን ይከጀላል፡፡
ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ (ለሰዎቹ) ምርጫ የላቸውም፡፡ አላህ ከማይግገባው ሁሉ ጠራ፡፡ ከሚያጋሯቸውም ላቀ፡፡
ጌታህም ልቦቻቸው የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡
እርሱም አላህ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ምስጋና በመጀመሪያይቱም በመጨረሻይቱም ዓለም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ ፍርዱም የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
አያችሁን (ንገሩኝ) «አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው አትሰሙምን» በላቸው፡፡
አያችሁን «አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው (ንገሩኝ) አታስተውሉምን» በላቸው፡፡
ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡
የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው» የሚልበትን (አስታውስ)፡፡
ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ (ያን ጊዜ) እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡
ቃሩን ከሙሳ ነገዶች ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ አመጸ፡፡ ከድልቦችም ያንን መከፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችን (ሸክሙ) የሚከብድን ሰጠነው፡፡ ወገኖቹ ለእርሱ አትኩራ፤ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና ባሉት ጊዜ (አስታውስ)፡፡
«አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» (አሉት)፡፡
(ሀብቱን) «የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው አለ፡፡ አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኀይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን (ሀብትን) በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መኾኑን አያውቅምን አመጸኞችም ከኀጢኣቶቻቸው (ምሕረት የሚከተለውን ጥያቄ) አይጠየቁም፡፡
በሕዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ኾኖ ወጣ፡፡ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ብጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና» አሉ፡፡
እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ለአመነ ሰው መልካምንም ለሠራ በላጭ ነው፡፡ ታጋሾችም እንጅ ሌላው አያገኛትም» አሉ፡፡
በእርሱም በቤቱም ምድርን ደረባን፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ጭፍሮች ምንም አልነበሩትም፡፡ ከሚርረዱትም አልነበረም፡፡
እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ አላህ በእኛ ላይ (በእምነት) ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር፡፡ ወይ ጉድ! ከሓዲዎች አይድኑም» የሚሉ ኾነው አነጉ፡፡
ይህች የመጨረሻይቱ አገር ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመፅን ለማይፈልጉት እናደርጋታለን፡፡ ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡
በደግ ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አልለው፡፡ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፡፡
ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ኾኖ ባንተ ላይ ያወረደው (አምላክ) ወደ መመለሻ (ወደመካ) በእርግጥ መላሽህ ነው፡፡ «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውን ሰውና እርሱም በግልጽ ስሕተት ውስጥ የኾነውን ሰው ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
መጽሐፉ ወዳንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ (ተወረደልህ)፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን፡፡
ከአላህም አንቀጾች ወዳንተ ከተወረዱ ጊዜ በኋላ አያግዱህ፡፡ ወደ ጌታህም (ሰዎችን) ጥራ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትኹን፤
ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
Icon