ترجمة سورة محمد

Sadiq and Sani - Amharic translation
ترجمة معاني سورة محمد باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation .


እነዚያ የካዱ ከአላህ መንገድም የከለከሉ (አላህ) ሥራዎቻቸውን አጠፋባቸው፡፡

እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመኾናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የኾነን እውነት ስለተከተሉ ነው፡፡ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል፡፡

እነዚያንም የካዱትን (በጦር ላይ) ባገኛችሁ ጊዜ ጫንቃዎችን በኀይል ምቱ፡፡ ባደካማችኋቸውም ጊዜ (አትግደሏቸው ማርኳቸው)፡፡ ማሰሪያውንም አጥብቁ፡፡ በኋላም ወይም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ፤ ወይም ትበዧቸዋላችሁ፡፡ (ይህም) ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው፡፡ (ነገሩ) ይህ ነው፡፡ አላህም ቢሻ ከእነርሱ (ያለጦር) በተበቀለ ነበር፡፡ ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)፡፡ እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡

በእርግጥ ይመራቸዋል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡

እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡

ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡

የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት (ከሓዲዎች) መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ያዩ ዘንድ በምድር ለይ አልኼዱምን? አላህ በእነርሱ ላይ (ያላቸውን ሁሉ) አጠፋባቸው፡፡ ለከሐዲዎችም ሁሉ ብጤዎችዋ አልሏቸው፡፡

ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ስለኾነና ከሓዲዎችም ለእነርሱ ረዳት ስለሌላቸው ነው፡፡

አላህ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባቸዋል፡፡ እነዚያም የካዱት (በቅርቢቱ ዓለም) ይጣቀማሉ፡፡ እንስሳዎችም እንደሚበሉ ይበላሉ፡፡ እሳትም ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት፡፡

ከከተማም እርሷ ከዚያች ካወጣችህ ከተማህ ይበልጥ በኀይል ጠንካራ የኾነች (ባለቤቶችዋን) ያጠፋናቸው ብዙ ናት፡፡ ለእነርሱም ረዳት አልነበራቸውም፡፡

ከጌታው በኾነች አስረጅ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ሥራቸው ለእነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን?

የዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት፡፡ ለእነርሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው፡፡ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ እንደኾነ ሰው፣ ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደቆራረጠው ነውን? (አይደለም)፡፡

ከእነርሱም ወዳንተ የሚያዳምጡ አልሉ፡፡ ከአንተም ዘንድ በወጡ ጊዜ ለእነዚያ ዕውቀት ለተሰጡት «አሁን ምን አለ?» ይላሉ፡፡ እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው፡፡

እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው፡፡

ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተወል፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?

እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህም መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡

እነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) «ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡

ታዛዥነትና መልካም ንግግር (ይሻላቸዋል) ትዕዛዙም ቁርጥ በኾነ ጊዜ ለአላህ (ትዕዛዝ) እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡

ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ ያደነቆራቸውም፣ ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው፡፡

ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?

እነዚያ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን ሸለመላቸው፡፡ ለእነርሱም አዝዘናጋቸው፡፡

ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊል እንታዘዛችኋለን» ያሉ በመኾናቸው ነው፡፡ አላህም መደበቃቸውን ያውቃል፡፡

መላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲኾኑ በገደሉዋቸው ጊዜ (ኹኔታቸው) እንዴት ይኾናል?

ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ስለ ተከተሉ ውዴታውንም ስለ ጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ሥራዎቻቸውን አበላሸባቸው፡፡

እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው አላህ ቂሞቻቸውን አለማውጣቱን ጠረጠሩን?

በሻንም ኖሮ እነርሱን ባሳየንህና በምልክታቸውም በእርግጥ ባወቅሃቸው ነበር፡፡ ንግግርንም በማሸሞራቸው በእርግጥ ታውቃቸዋለህ፡፡ አላህም ሥራዎቻችሁን ያውቃል፡፡

ከእናንተም ታጋዮቹንና ታጋሾቹን እስከምናውቅ፣ ወሬዎቻችሁንም እስከምንገልጽ ድረስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡

እነዚያ የካዱና ከአላህም መንገድ ያገዱ ለእነርሱም ቅኑ መንገድ ከተገለጸላቸው በኋላ መልክተኛውን የተከራከሩ አላህን በምንም አይጎዱትም፡፡ ሥራዎቻቸውንም በእርግጥ ያበላሻል፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡

እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ ያገዱ፣ ከዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው የሞቱ አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም፡፡

እናንተም አሸናፊዎቹ ስትኾኑ አላህ ከእናንተ ጋር ሲሆን አትድከሙ፡፡ ወደ ዕርቅም አትጥሩ፡፡ ሥራዎቻችሁንም ፈጽሞ አያጎድልባችሁም፡፡

ቅርቢቱ ሕይወት ጫወታና ዛዛታ ብቻ ናት፡፡ ብታምኑም ብትጠነቀቁም ምንዳዎቻችሁን ይሰጣችኋል፡፡ ገንዘቦቻችሁንም (ሁሉ) አይጠይቃችሁም፡፡

እርሷን ቢጠይቃችሁና ችክ ቢልባችሁ ትሰስታላችሁ፡፡ ቂሞቻችሁንም ያወጣል፡፡

ንቁ! እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጥጠሩ ናችሁ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የሚሰስት ሰው አልለ፡፡ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡
Icon