سورة ص

الترجمة الأمهرية

የሱራ ص ትርጉም በالأمهرية ከالترجمة الأمهرية

الترجمة الأمهرية

ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡
ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡
ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡
ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም «ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው» አሉ፡፡
«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው» (አሉ)፡፡
ከእነርሱም መኳንንቶቹ «ሂዱ፤ በአማልክቶቻችሁም (መግገዛት) ላይ ታገሱ፡፡ ይህ (ከእኛ) የሚፈለግ ነገር ነውና» እያሉ አዘገሙ፡፡
«ይህንንም በኋለኛይቱ ሃይማኖት አልሰማንም፡፡ ይህ ውሸትን መፍጠር እንጅ ሌላ አይደለም» (እያሉም)፡፡
«ከመካከላችን በእርሱ ላይ ቁርኣን ተወረደን?» (አሉ)፡፡ በእውነት እነርሱ ከግሳጼዬ (ከቁርኣን) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡
ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?
ወይስ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የእነርሱ ነውን? (ነው ቢሉ) በመሰላሎችም ይውጡ፡፡
እዚያ ዘንድ ከአሕዛብ የሆኑ ተሸናፊ ሰራዊት ናቸው፡፡
ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድም፣ የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባበሉ፡፡
ሰሙድም፣ የሉጥ ሰዎችም፣ የአይከት ሰዎችም (አስተባበሉ)፡፡ እነዚህ አሕዛቦቹ ናቸው፡፡
ሁሉም መልክተኞቹን ያስዋሹ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ ቅጣቴም ተረጋገጠባቸው፡፡
እነዚህም ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲትን ጩኸት እንጅ ሌላን አይጠባበቁም፡፡
«ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት መጽሐፋችንን አስቸኩልልን» አሉም፡፡
በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡
እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋድም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆኑ ገራንለት፡፡
በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው (ገራንለት)፡፡ ሁሉም ለእርሱ (ማወደስ) የሚመላለስ ነው፡፡
መንግሥቱንም አበረታንለት፡፡ ጥበብንም ንግግርን መለየትንም ሰጠነው፡፡
የተከራካሪዎቹም ወሬ መጥቶልሃልን? ምኩራቡን በተንጠላጠሉ ጊዜ፡፡
«ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፡፡ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው» አለ፡፡ ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡
ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ ዝንባሌሀንም አትከተል፤ከአላህ መንገድ ያሳሳትሃልና፡፡ እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡
ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!
በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን?
(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡
ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! (ሱለይማን)፣ እርሱ መላሳ ነው፡፡
በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሦስት እግሮችና በአራተኛዋ ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌዎች ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (አስታውስ)፡፡
አለም «እኔ (ፀሐይ) በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ፡፡»
«በእኔ ላይ መልሷት» (አለ) አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም ማበስ ያዘ፡፡
ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ አካልን ጣልን፡፡ ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ፡፡
ነፋስንም በትእዛዙ ወደፈለገበት ስፍራ ልዝብ ኾና የምትፈስ ስትኾን ገራንለት፡፡
Verse 37
ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰጣሚዎችን ሁሉ (ገራንለት)፡፡
Verse 38
ሌሎችንም በፍንጆች ተቆራኞችን (ገራንለት)፡፡
«ይህ ስጦታችን ነው፡፡ ያለግምት ለግስ፤ ወይም ጨብጥ» (አልነው)፡፡
ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ፤ መልካም መመለሻም በእርግጥ አልለው፡፡
ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡
«በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው» (ተባለ)፡፡
ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡
«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡
ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡
እኛ ጥሩ በኾነች ጠባይ መረጥናቸው፡፡ (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡
እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው፡፡
ኢስማዒልንም፣ አልየሰዕንም፣ ዙልኪፍልንም አውሳ፡፡ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡
ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ ለአላህ ፈሪዎችም በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው፡፡
በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲኾኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡
በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ኾነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ፡፡
እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች እኩያዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተሰፋ ነው፡፡
ይህ (ለአማኞች ነው)፡፡ ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው፡፡
Verse 56
የሚገቧት ስትኾን ገሀነም (አለቻቸው)፡፡ ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች፡፡
Verse 57
ይህ (ለከሓዲዎች ነው)፡፡ ይቅመሱትም፡፡ የፈላ ውሃና እዥ ነው፡፡
ይህ ከእናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ጭፍራ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ለእነርሱ አይስፋቸው፡፡ እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)፡፡
(ተከታዮቹ) ይላሉ «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ፡፡ እናንተ (ክህደቱን) ለእኛ አቀረባችሁት፡፡ መርጊያይቱም (ገሀነም) ከፋች፡፡»
«ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ እጥፍን ቅጣት ጨምርለት» ይላሉ፡፡
ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች (እዚህ) አናይምሳ፡፡»
«መቀለጃ አድርገን ያዝናቸውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነሱ ዋለሉ?»
ይህ በእርግጥ እምነት ነው፡፡ (እርሱም) የእሳት ሰዎች (የእርስ በእርስ) መካሰስ ነው፡፡
«የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡»
Verse 67
በላቸው «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው፡፡
Verse 68
«እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
(በአደም ነገር) «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡
«ወደእኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝም» (በል)፡፡
«ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» (አልኩ)፡፡
Verse 73
መላእክትም መላውም ባንድነት ሰገዱ፡፡
ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ኮራ፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡
(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡
(አላህ) አለው «ከእርሷ ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና፡፡»
«እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን፡፡»
«ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝም» አለ፡፡
Verse 80
(አላህም) አለው «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡»
Verse 81
«እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡»
Verse 82
(እርሱም) አለ «በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡»
Verse 83
«ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡»
Verse 84
(አላህ) አለው «እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡
ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡»
በላቸው «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም፡፡
«እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
Verse 88
«ትንቢቱንም (እውነት መኾኑን) ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡»
تقدم القراءة