ترجمة سورة هود

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة هود باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡
(እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ፡፡»
ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፡፡ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፡፡ ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡
መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
ንቁ! እነሱ ከእርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ፡፡ ንቁ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፡፡ የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው)፡፡ «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም ይላሉ፡፡
ቅጣቱንም ወደ ተቆጠሩ (ጥቂት) ጊዜያቶች ከእነርሱ ብናቆይላቸው «(ከመውረድ) የሚከለክለው ምንድን ነው» ይላሉ፡፡ ንቁ! በሚመጣባቸው ቀን ከእነሱ ላይ ተመላሽ አይደለም፡፡ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም (ቅጣት) በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል፡፡
ሰውንም ከእኛ ችሮታን ብናቀምሰው ከዚያም ከርሱ ብንወስዳት እርሱ በእርግጥ ተስፋ ቆራጭ ክህደተ ብርቱ ነው፡፡
ካገኘችውም ችግር በኋላ ጸጋዎችን ብናቀምሰው «ችግሮች ከኔ ላይ በእርግጥ ተወገዱ» ይላል (አያመሰግንም)፡፡ እርሱ ተደሳች ጉረኛ ነውና፡፡
ግን እነዚያ የታገሱ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለእነሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡
በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፡፡ አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው፡፡
ይልቁንም «(ቁርኣንን) ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ ሱራዎች አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን (ረዳት) ጥሩ» በላቸው፡፡
ለእናንተም (ጥሪውን) ባይቀበሏችሁ የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ዕወቁ፡፡ ታዲያ እናንተ የምትሰልሙ ናችሁን (ስለሙ በላቸው)፡፡
ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፤
እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡
ከጌታው ከአስረጅ ጋር የኾነ ሰው፤ ከእርሱም (ከአላህ) የኾነ መስካሪ የሚከተለው፣ ከእርሱ በፊትም የሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲኾን (የመሰከረለት) የቅርቢቱን ሕይወት እንደሚሻው ሰው ነውን እነዚያ በእርሱ (በቁርኣን) ያምናሉ፡፡ ከአሕዛቦቹም በእርሱ የሚክድ ሰው እሳት መመለሻው ናት፡፡ ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፡፡ እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡
በአላህ ላይ እብለትን ከሚቀጣጥፍም ይበልጥ በዳይ ማነው እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀርባሉ፡፡ መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው» ይላሉ፡፡ ንቁ! የአላህ ርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን፡፡
(እነሱም) እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚከለክሉ መጥመሟንም የሚፈልጓት ናቸው፡፡ እነሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነሱ ከሓዲዎች ናቸው፡፤
እነዚያ በምድር ውስጥ (ከአላህ) የሚያመልጡ አልነበሩም፡፡ ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸውም፡፡ ለእነሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል፡፡ (እውነትን) መስማትን የሚችሉ አልነበሩም የሚያዩም አልነበሩም፡፡
እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋቸው ናቸው፡፡
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ እነሱ መሆናቸው ጥርጥር የለውም፡፡
እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ እንደ ዕውርና እንደ ደንቆሮ እንደሚያይና እንደሚሰማም ብጤ ነው፡፡ በምሳሌ ይተካከላሉን አትገሰጹምን
ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፡፡ (አላቸውም)፡- «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ነኝ፡፡»
«አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና፡፡»
ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት መሪዎቹ ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም፡፡ እነዚያም እነሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም፡፡ ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም፡፡ ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን አሉ፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ (ነብይነት) ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለርቯ ጠይዎች ስትሆኑ እርቯን (በመቀበል) እናስገድዳችኋለን» አላቸው፡፡
«ሕዝቦቼም ሆይ! በርሱ (በተላክሁበት ማድረስ) ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ እኔም እነዚያን ያመኑትን አባራሪ አይደለሁም፡፡ እነርሱ ጌታቸውን የሚገናኙ ናቸውና፡፡ ግን እኔም የምትሳሳቱ ሕዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ፡፡»
«ሕዝቦቼም ሆይ ባባርራቸው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማን ነው አትገሰጹምን»
«ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም፡፡ እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም፡፡ ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን (እምነትን) አይሰጣቸውም አልልም፡፡ አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና» (አላቸው)፡፡
«ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን፡፡ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፡፡ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው» አሉ፡
«እርሱን የሚያመጣባችሁ የሻ እንደ ሆነ አላህ ብቻ ነው፡፡ እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም» አላቸው፡፡
«ለእናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ኾነ ምክሬ አይጠቅማችሁም፡፡ እርሱ ጌታችሁ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ» (አላቸው)፡፡
«ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን ብቀጥፈው ኃጢኣቴ (ቅጣቱ) በኔ ላይ ነው፡፡ እኔም ከምታጠፉት (ጥፋት) ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
ወደ ኑሕም እነሆ «ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት) አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን ማለት ተወረደ፡፡»
(አላህም) «በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ መርከቢቱን ሥራ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ ሰማጮች ናቸውና» (አለው)፡፡
ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር ከእርሱ እየተሳለቁ መርከቢቱን ይሠራል፡፡ «ከእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን ከናንተ እንሳለቅባችኋለን» አላቸው፡፡
«የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበት ሰው (ማን እንደ ሆነ) ወደፊት ታውቃላችሁ» (አላቸው)፡፡
ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ፤ ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡
«መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው እያላችሁም በውስጧ ተሳፈሩ፡፡ ጌታ መሓሪ አዛኝ ነውና» አላቸው፡፡
እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡
(ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ፡፡ (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው፡፡ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፡፡ ከሰጣሚዎቹም ሆነ፡፡
ተባለም፡- «ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ፡፡ ውሃውም ሰረገ፡፡ ቅጣቱም ተፈጸም፡፡ ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች፡፡ ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ)» ተባለ፡፡
ኑሕም ጌታውን ጠራ፡፡ አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡ ኪዳንህም እውነት ነው፡፡ አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ፡፡»
(አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡
«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ» አለ፡፡
«ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፡፡ (ከእነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን፡፡ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል» ተባለ፡፡
ይህቺ ከሩቁ ወሬዎች ናት፡፡ ወደ አንተ እናወርዳታለን፡፡ አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም፡፡ ታገስም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና፡፡
ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን (ላክን)፡፡ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ አታውቁምን
«ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፡፡ ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና፡፡ ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል፡፡ አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ፡፡»
አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም፡፡ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፡፡ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም፡፡
«ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም» (አሉ)፡፡ «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ፡፡ ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ» አላቸው፡፡
ከእርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ)፡፡ ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ፡፡
«እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ፡፡ በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ፡፡ ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው» (አላቸው)፡፡
«ብትዞሩም በእርሱ ወደእናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ፡፡ ጌታዬ ከእናንተ ሌላ ሕዝብም ይተካል ምንም አትጎዱትምም፡፡ ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና» (አላቸው)፡፡
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው፡፡
ይህች (ነገድ) ዓድ ናት፡፡ በጌታቸው ታምራት ካዱ፡፡ መልክተኞቹንም አመጹ፤ የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ፡፡
በዚህች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ፡፡ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፡፡ ንቁ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ፡፡ ንቁ! የሁድ ሕዝቦች ለሆኑት ዓዶች (ከእዝነት) መራቅ ይገባቸው፡፡
ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው፡፡
«ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው፡፡
ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት፡፡ ተውዋትም፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» (አላቸው)፡፡
ወግተው ገደሏትም፡፡ (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ፡፡ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው፡፡
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን፡፡ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፡፡ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና፡፡
እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ የተንበረከኩ ሆነው ሞተው አነጉ፡፡
በእሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ፡፡ ንቁ! ለሰሙዶች (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡
መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡
እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡
ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡
(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፡፡
«ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡
ከኢብራሂም ፍራቻው በሌደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር) ይከራከረን ጀመር፡፡
ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ ነውና፡፡
«ኢብራሂም ሆይ! ከዚህ (ክርክር) ተው፡፡ እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል፡፡ እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው» (አሉት)፡፡
መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ፡፡
ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት፡፡ ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው፤ (አግቧቸው)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን» አላቸው፡፡
«ከሴቶች ልጆችህ ለእኛ ምንም ጉዳይ የለንም፡፡ አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ» አሉት፡፡
«በእናንተ ላይ ለኔ ኀይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)» አላቸው፡፡
«ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፡፡ (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም፡፡ ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሊድ፡፡ ከእናንተም አንድም (ወደኋላው) አይገላመጥ፡፡ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እነሆ እርሷን (እነሱን) የሚያገኛቸው ስቃይ ያገኛታልና፡፡ ቀጠሯቸው እንጋቱ ላይ ነው፡፡ ንጋቱ ቅርብ አይደለምን» አሉት፡፡
|ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ (ከተማይቱን) ላይዋን ከታችዋ አደረግን (ገለበጥናት)፡፡ ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን፡፡
ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)፡፡ እርሷም ከበደለኞቹ ሩቅ አይደለችም፡፡
ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን (ላክን)፡፡ አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፡፡ እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ፡፡
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡
አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡»
«ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣዖታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን (እንድንተው) ታዝሃለችን አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑ አንተ ነህና» አሉት፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ፤ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ብሆንና ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ (በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን) ከእርሱ ወደ ከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡ በተቻለኝ ያክል ማበጀትን እንጂ አልሻም (ለደግ ሥራ) መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ወደእርሱም እመለሳለሁ፤» አላቸው፡፡
«ወገኖቼም ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑሕን ሕዝቦች ወይም የሁድን ሕዝቦች ወይም የሷሊሕን ሕዝቦች ያገኛቸው (ቅጣት) ብጤ እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ፡፡ የሉጥም ሕዝቦች ከእናንተ ሩቅ አይደሉም፡፡
«ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)፡፡
«ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀውም፡፡ እኛም አንተን በእኛ ውስጥ ደካማ ሆነህ እናይሃለን፡፡ ጎሳዎችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር፤ አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም» አሉት፡፡
«ሕዝቦቼ ሆይ! ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን (አላህን) ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አድርጋችሁም ያዛችሁት፡፡ ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው» አላቸው፡፡
«ሕዝቦቼም ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ፡፡ እኔ ሠሪ ነኝና፡፡ የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደኾነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡ ጠብቁም እኔ ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና»(አላቸው)፡፡
ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ፡፡
በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙድ (ከአላህ እዝነት) እንደ ራቀች መድየንም ትራቅ፡፡
ሙሳንም በተዓምራታችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው፡፡
ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ (ላክነው)፡፡ የፈርዖንንም ነገር (ሕዝቦቹ) ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም፡፡
በትንሣኤ ቀን ሕዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ወደ እሳትም ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ!
በዚችም (በቅርቢቱ ዓለም) እርግማንን አስከተልናቸው፡፡ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፡፡ የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!
ይህ (የተነገረው) ከከተሞቹ ወሬዎች ነው፡፡ ባንተ ላይ እንተርከዋለን፡፡ ከእርሷ ፋናው የቀረና ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ አለ፡፡
እኛም አልበደልናቸውም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ፡፡ የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸው አማልክቶቻቸው በምንም አላዳኗቸውም፡፡ ከማክሰርም በቀር ምንም አልጨመሩላቸውም፡፡
የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው፡፡ ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው፡፡
በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ ይህ (የትንሣኤ ቀን) ሰዎች በርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው፡፡
(ይህንን ቀን) ለተቆጠረም ጊዜ እንጂ አናቆየውም፡፡
በሚመጣ ቀን ማንኛዋም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም፡፡ ከነሱም መናጢና ዕድለኛም አልለ፡፡
እነዚያ መናጢ የሆኑትማ፡ በእሳት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው፡፡
ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውተሪዎች ሲኾኑ (በእሳት ይኖራሉ)፡፡ ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና፡፡
እነዚያም ዕድለኞቹማ ጌታህ ከሻው (ጭማሬ) ሌላ ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ኾነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የማይቋረጥ ስጦታን ተሰጡ፡፡
እነዚህ (ከሓዲዎች) ከሚገዙት ጣዖት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን፤ አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚግገዙት እንጂ አይግገዙም፡፡ እኛም (እነዚህን) ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን፡፡
ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በእርሱም ተለያዩበት፡፡ ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) ይፈረድ ነበር፡፡ እነሱም ከእርሱ (ከቁርኣን) አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን (ምንዳቸውን) በእርግጥ ይሞላላቸዋል፡፡ እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነውና፡፡
እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡
ወደእነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረድዱም፡፡
ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡
ታገስም፤ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና፡፡
ከእናንተም በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ቀሪ ሥራዎች ባለቤቶች ለምን አልነበሩም ግን ከእነሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ (ከለከሉና ዳኑ)፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች (አልከለከሉም)፡፡ በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ፡፡ አመጸኞችም ነበሩ፡፡
ጌታህም ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም፡፡
ጌታህም በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ሕዝብ ባደረጋቸው ነበር፡፡ የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም፡፡
ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (ከመለያየት አይወገዱም)፡፡ ለዚሁም ፈጠራቸው፡፡ የጌታህም ቃል ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ በማለት ተፈጸመች፡፡
ከመልክተኞቹም ዜናዎች (ተፈላጊውን) ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም (ሱራ) እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡
ለእነዚያም ለማያምኑት ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ፤ እኛ ሠሪዎች ነንና በላቸው፡፡
ተጠባበቁም እኛ ተጠባባቂዎች ነንና (በላቸው)፡፡
በሰማያትና በምድርም ያለው ምስጢር ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉም ወደርሱ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ ተገዛው፡፡ በእርሱም ላይ ተጠጋ፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
Icon