ترجمة سورة الغاشية

الترجمة الأمهرية
ترجمة معاني سورة الغاشية باللغة الأمهرية من كتاب الترجمة الأمهرية .
من تأليف: محمد صادق ومحمد الثاني حبيب .

የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡
Icon