ترجمة معاني سورة المزّمّل باللغة الأمهرية من كتاب Sadiq and Sani - Amharic translation

Sadiq and Sani - Amharic translation

آية رقم 1


አንተ ተከናናቢው ሆይ፡፡
آية رقم 2

ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ (ስገደ)፡፡
آية رقم 3

ግማሹን (ቁም)፤ ወይም ከርሱ ጥቂትን ቀንስ፡፡
آية رقم 4

ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፡፡ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ፡፡
آية رقم 5

እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና፡፡
آية رقم 6

የሌሊት መነሳት እርሷ (ሕዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ናት፡፡ ለማንበብም ትክክለኛ ናት፡፡
آية رقم 8

የጌታህንም ስም አውሳ፤ ወደእርሱም (መግገዛት) መቋረጥን ተቋረጥ ፡፡

(እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡
آية رقم 10

(ከሓዲዎች) በሚሉትም ላይ ታገሥ፡፡ መልካምንም መተው ተዋቸው፡፡
آية رقم 11

የድሎት ባለቤቶችም ከኾኑት አስተባባዮች ጋር ተዎኝ፡፡ ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው፡፡
آية رقم 12

እኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎች እሳትም አልለና፡፡
آية رقم 13

የሚያንቅ ምግብም፤ አሳማሚ ቅጣትም (አልለ)
آية رقم 14

ምድርና ገራዎች በሚርገፈገፉበት፣ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚኾኑበት ቀን፡፡

እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መልክተኛን ወደእናንተ ላክን፡፡ ወደ ፈርዖን መልክተኛን እንደላክን፡፡
آية رقم 16

ፈርዖንም መልክተኛውን አመጸ፤ ብርቱ መያዝንም ያዝነው፡፡
آية رقم 17

ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡
آية رقم 18

ሰማዩ በርሱ (በዚያ ቀን) ተሰንጣቂ ነው፡፡ ቀጠሮው ተፈጻሚ ነው፡፡

አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መኾንህን ጌታህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ከእነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች (የሚቆሙ መኾናቸውን ያውቃል)፡፡ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይለክካል፡፡ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተ ላይም (ወደ ማቃለል) ተመለሰላችሁ፡፡ ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፡፡ ከእናንተ ውስጥ በሽተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፡፡ (አቃለለላቸውም)፡፡ ከእርሱም የተቻለችሁን አንብቡ፡፡ ሶላትንም ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፡፡ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
تقدم القراءة